You are here: HomeOpinionsየሙጋቤ ሎጂክ ፡- የእውነት መለኪያ ፣ ልምምድ

የሙጋቤ ሎጂክ ፡- የእውነት መለኪያ ፣ ልምምድ

Written by  Wednesday, 08 July 2015 00:00

የአሜሪካውን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ተከትሎ እንደ ልማዳችን ሰሞኑን በግብረ ሰዶማውያን እና በግብረ ሰዶማዊነት ዙሪያ አቧራው ጨሰ እያልን ነው፡፡  አንዳንዶች ፣ አንፃራዊ በሆነ መልኩ ስክነት እና ማስተዋል የሚታይበት ጽሁፍ የጻፉ ሲሆን፡፡ ሌሎቹ ደግሞ፣ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወሰነው ይመስል ጉዳዩ የሚመለከታቸውንም የማይመለከታቸውንም በጥቅስ ሲጎሽሙ የከረሙት፡፡ የእኛ ባንዲራ በእነሱ ሰልፍ ላይ ተውለበለብ ብሎ አረፋ እየደፈቀ ያወራኝ ወዳጄ «እንኳን ከጨረቃ ወደ ምድር በሰላም ተመለስክ!» ብዬዋለሁ፡፡ ለማንኛውም ይሄ የቁጣ ነበልባል ሐገራችን ውስጥ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን መላው አፍሪካን ያዳረሰ ነበር፡፡ ከአሰተያየት ሰጪዎቹ ዝነኛው የአፍሪካ ኀብረት የወቅቱ ሊቀ መንበር ሮበርት ሙጋቤ ዋነኛው ናቸው፡፡

 

አዛውንቱ አፍሪካዊ መሪ ሮበርት ሙጋቤ ሰሞኑን የአሜሪካን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ተከትሎ የግብረ ሰዶማውያን ጉዳይ ላይ ለሐገራቸው ሬዲዮ ሰሰጡት መግለጫ  ቅንጫቢ ይሄ ነው፡፡

 

በእኔ ድምዳሜ መሠረት ፕሬዚዳንት ኦባማ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ስለሚያበረታታ፣ ግብረ ሰዶማውያንን ስለሚደግፍ  ደስ የሚያሰኝ ገጽታም ስለሚስበው ፤ አስፈላጊ ከሆነ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ሄጄ ፣ በጉልበቴ ተንበርክኬ አባማን ለጋብቻ እጠይቀዋለሁ፡፡

 

ጎበዝ ሰሞኑን «የኦባማን ውሳኔ» እና የኦባማን ጉብኝት እያላሰልኩ ማህበራዊ ድረ ገጾችን ሳገላብጥ ባለፉት ሣምንታት ውስጥ እንደዚች ዐረፍተ ነገር ተደጋግሞ የተለጠፈ ነገር የለም፡፡ ይህችን ሐረግ የእኛ ሐገር ፌስቡካውያን በአማርኛ ተርጉመው በየቦታው ለጥፈዋታል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ሳነባት በሳቅ ፍርስ እንዳልኩ አልደብቃችሁም፡፡ ትንሽ ቆየት ብዬ ሳስብ ግን ሰውየው ይህንን ብቻ ካሉ አስተሳሰባቸውን ጥያቄ ውስጥ መክተቴ አልቀርም፡፡ የአዲስ ነገር አዘጋጅ የነበረው መሥፍን ነጋሽ «በሙጋቤ እና በፑቲን የሞራል አርአያነት የሚነቃቃ ትውልድ» (ፌስ ቡክ ገጹ ላይ እንደለጠፈው) ያለውን ሳስብ ደግሞ ምናለበት የእኚህን አዛውንት ስህተት ባሳይ የሚል ወኔ ቢጤ ያዘኝ፡፡

 

ይህች የሙጋቤ ንግግር በራሷ አሳሳች ናት፡፡ ምንም እንኳን አሳሳችነቷ ንግግሯን በተናገሩበት ዐውድ ውስጥ ቢቀንስም ሙጋቤ ግን የሳቸውን ልምምድ የእውነት መለኪያ እያደረጉ ነው፡፡ እንዴት አትሉኝም ?እሰቲ የሙጋቤን ሐሳብ በሚገባን መልኩ እናስቀምጠው ፡-

 

  • ሀ. ግብረ ሰዶማዊነት ትክክል ነው ብሎ የሚያምን ሰው ሁሉ ግብረ ሰዶማዊ መሆን አለበት፡፡
  • ለ. ኦባማ ግብረ ሰዶማዊነት ትክክል ነው ብሎ ያምናል፡፡
  • ሐ. ስለዚህ፣  አባማ እምነቱን  ወንድ በማግባት(ሙጋቤ) ማሳየት አለበት፡፡

 

ሙጋቤ ያሉን ይህንን ነው፡፡ (ከተሳሰትኩ እታረማለሁ፡፡) አንደኛ ፣ ግብረ ሰዶማዊነት ትክክል ነው ብሎ የሚያምን ሰው ሁሉ፣ ግብረ ሰዶማዊ መሆን አለበት የሚለው ሐሳብ ስህተት ነው፡፡ ስለ ሐጢአት ክፋት ለማውራት የግድ ሐጢአተኛ መሆን ያስፈልጋል እንዴ! የሞትን እውነተኛነት ለማረጋገጥ የግድ መሞት ያፈልገን ይሆን፡፡ የአንድን ነገር እውነትን የሚለካው በግለሰቡ ልምምድ ላይ ነው እንዴ?  እርገጠኛ ነኝ መጽሐፍ ቅዱስ የሚፈቅዳቸውን እና የሚከለክላቸውን ነገሮች የማናደርገው ከልምምዳችን በመነሳት አይመስለኝም፡፡ እግዚእብሔር አፍቃሪ እና እውነተኛ አምላክ ነው፣ ማንነቱን እና ሥራው በቃሉ ገልጧል ፡፡ ቃሉ ደግሞ እውነት ነው፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል የሚለን ሁሉ እውነት ነው፡፡ (ልምምዳችን ቢያረጋግጠውም ባያረጋግጠውም)፡፡ 

 

ሁለተኛ ፣ ሁሉ ይቀርና ኦባማ  ነሸጥ አድርጎት «ለአፍሪካ ኀብረት ስብሰባ እገረ መንገዴን ስሄድ ሙጋቤን አገባለሁ፡፡ ደሞ ለጋብቻ ጠይቆኝ ቢልስ፡፡» አዛውነቱ ሙጋቤ እንዳሉት ግብረ ሰዶማዊነት ትክክል ሊሆን ነው፡፡ በፍጹም፡፡

 

ስለዚህ ሙጋቤ ያቀረቡትን (ተነጥሎ የተጠቀሰ) ስሜታዊ እና የተሳሳተ ሙግት ግብረ ሰዶማዊነት ለመቃወም የቀረበ አይነተኛ ሙግት አድርጎ ማቅረብም ሆነ መለጠፍም ሆን ማስለጠፍ ተገቢ አይመስለኝም፡፡

Read 7159 times Last modified on Thursday, 09 July 2015 06:17
Abinet Ababu

I am Abinet Ababu a disciple, a husband and a father of two. A graduate of for Evangelical Theological college (ETC) in Bible Translation and Literacy. A student at at Africa Nazarene University (Nairobi, Kenya). A Bible school teacher, speaker and writer. An Interpreter by trade (to Amharic,English to Ormiffa -pending). 

Website: abinetababu.wordpress.com Email This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

Nahu's Corner

 

 

 

.

Right Now

We have 53 guests and no members online

About Us

Semayawi Thought is an online magazine published in Amharic and English, focused on contents to spiritual and personal growth.