You are here: HomeBekele Berhanu (MD)
Bekele Berhanu (MD)

Bekele Berhanu (MD)

ዶ/ር በቀለ ብርሃኑ በ1990 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሜዲካል ፋኩልቲ በኤም.ዲ ተመርቀዋል፡፡በተጨማሪም ቤልጂየም ውስጥ በሚገኝ አንድ ዩኒቨርሲቲ ለዐሥር ወራት የስትራቴጂክ ማኔጅመንት ኦፍ ሄልዝ ሰርቪስስ (strategic management of health services) ሥልጠና ተከታትለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት አሜሪካ ጌትስበርግ በመኖሪያቸው አቅራቢያ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል በሳምንት ሦስት ቀን ይሠራሉ፡፡ጌታን እያገለገሉ ከባለቤታቸው ከወይዘሮ አባይና ከሦስት ልጆቻቸው ጋር በአሜሪካን አገር በመኖር ላይ ይገኛሉ፡፡በ2014 አመተ ምሕረት የራሳቸውን ግለ-ታሪክ ጽፈዋል፡፡፡፡ርእሱም ከጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን የሚል ሲሆን በኢትዮጵያና በእዚህ በአገረ አሜሪካ በተለያዩ ቦታዎች እየተሸጠ ይገኛል፡፡እንዲሁም በዚህ በ2015 ዓ.ም ገጣሚው በሚል ርእስ የግጥም መድብል ለሕዝብ ንባብ አበርክተዋል፡፡በተጨማሪም በተለያዩ ድረ-ገጾችና ሶሻል ሜድያዎች የተለያዩ መጣጥፎችንና ግጥሞች በማበርከት ላይ ይገኛሉ፡፡

Email: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
በሮሜ ምዕራፍ 12፡1-2 ያለውን ክፍል ስንመለከት የተወደደ መሥዋዕት ማለት ለአእምሮ የሚመች አገልግሎት እንደ ሆነ ተገልጿል፡፡ለአእምሮ የሚመች አገልግሎት የሚለውን ሐሳብ የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱሶች “Reasonable service” ይሉታል፡፡ይህ ቃል የሚስማማ፣ የሚመጥን፣ አግባብነት ያለው ወዘተ የሚሉ ሐሳቦችን የያዘ ቃል ነው፡፡ለአእምሮ የሚመች አገልግሎት በተግባር ደረጃ ምን እንደሚመስል ከቁጥር 7 ጀምሮ እስከ 21 ድረስ ያሉትን በዝርዘር ማየት ይቻላል፡፡ እንዳውም ሌላ እስከማያስፈልግ ድረስ በሙላት ተሰድረዋል፡፡ የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል፡- ...
የእግዚአብሔር ኃይል ድንቅ ነው፡፡ ይህንን ኃይል የምንስበው ደግሞ ከቃሉ ጋር ባለን ቁርኝትና ጸሎት መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ነገር ግን እውነተኛ እግዚአብሔር ደስ የሚሰኝበት ጸሎት መጸለይ እንደ ቀላል መታየት የለበትም፡፡   አንደኛው ተግዳሮት የጨለማው ጥላ በጸሎት ላይ ያለ የሌለ ኃይሉን ስለሚያሳርፍ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ በተለይ በዚህ በምዕራቡ ዓለም ካለው የሥራ ጫናና ባተሌነት የተነሣ፣ ጉልበትን ለጸሎት ማጠፍ እጅግ ከባድ ነው፡፡ ከዚህም የተነሣ አንዳንዴ የጭለማው ዓለም ተጽዕኖ በሕይወታችን ላይ በግልጽ ይታያል፡፡   ከሚታወቁት ተጽዕ...

Most Read

ከእግዚአብሔር ጋር የሚሠራ...

Written bySolomon Abebe Gebremedhin

It is Okay not t...

Written byMeskerem T. Kifetew, PharmD

Lust On a Driver...

Written byMeskerem T. Kifetew, PharmD

የአገር ያለህ!...

Written byNegussie Bulcha

 

 

 

.

Right Now

We have 346 guests and no members online

About Us

Semayawi Thought is an online magazine published in Amharic and English, focused on contents to spiritual and personal growth.