You are here: HomeOpinionsሚዲያ ፣ ሕግና የወንጌላዊያኑ ማሕበረሰብ

ሚዲያ ፣ ሕግና የወንጌላዊያኑ ማሕበረሰብ

Written by  Monday, 27 October 2014 00:00

ከአጋንንት እስራት ነፃ እንደወጣችና ጌታን እንደተቀበለች የምትናገር አንዲት ስሟን የማልጠቀሳት ትምሕርት ቀመስ እህት በቴሌቪዥን ከአጋንንት እስራት ስትፈታ ለሕዝብ በመታየቷ በግል ሕይዋቷና በዕለት ለዕለት ኑሮዋ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደፈጠረባትና ማስታወቂያ እንደተሰራባት ከሰዎች መስማቷን ስትናገር ለማድመጥ ችያለሁ፡፡ ሐዱሽ የሚባል ሌላ በቅርቡ ጌታን ወደ ማወቅ የመጣ አንድ ወንድም በተመሳሳይ ያለፈቃዱና ያለ-እውቅናው በአንድ ቤተ እምነት የቴሌቪዥን ስርጭት ላይ መቅረቡን እንዳልወደደውና በዘመድና በሚያውቃቸው ዘንድ ላልተዘጋጀበት ትችት እንደዳረገው በግል አጫዉቶኛል፡፡ ሌላም መሰል ታሪኮችን መስማታቸንን እንቀጥላለን ፤ አንዳዱ ሲያሸማቅቀን ሌላው ሲያሰቀን ፤ ጎንበስ ቀና እያልን ከሚዲያው ዓለም ጋር እኛም (እንደ ማሕበረ ምዕመናን) የሚዲያውን ዓለም የምናሰተዳደርበትና የምንቃኝበትን እውቀትና ክሕሎት ሳናዳብር ፤ ከሚዲያው ዓለም እየዋኘን ፤ ሚዲያውን ይዘነዋል፡፡

 

በተለያየ ቤተ እምነቶች በመገኘት የዘወትር አምልኮተ አምላክን ለማከናወንና ለልዩ ልዩ መርሐ ግብር ወደ መሰብሰቢያ አዳራሾች የሚሄደው ማሕበረ አማንኒያን ፤ በቤተእምነቱ የሚዲያ ሥርጭት ላይ ተቀርጾና ተቀናብሮ በማሰራጫ አውታሮች እንደሚቀርብ አውቆና ተገንዝቦ የሚደረግ ባለመሆኑ ፤ የተለያዩ ግለሶችን በተለየም ታዋቂና በሕዝብ ዘንድ ከበሬታ ያለቸውን ሰዎች ለግልና የቤተ እምነቱን መርሐ ግብሮች ማሻሻጫነት ሊጠቀሙበት እንደሚችሉና እየተጠቀሙበት አንደሆነ የዚህ አይነት ጥቃት ሰለባ የሆኑ አማኞች ይናገራሉ፡፡

 

በኢትዮጰያ ውስጥ የሚዲያ ሕግ እንዳለ የሚያውቅ ፣ ያለ ግለሰቡ ዕውቅና በምንም ሁኔታ ተንቀሳቃሽ ምስልን ሆነ ፎቶ ግራፍ በሚዲያ ለትርፍ ይሁን ትርፍ ለማያሰገኝ የትኛውም አግልግሎት ማዋል እንደማይችል ይደነግጋል፡፡ ጥያቄው የኛ ሚዲያ ባለንብረቶች ይህን ሕግ ያውቁታል ወይ የሚል ብቻ ነው? ሰዎች ቀስ በቀስ ያለ ግንዜቤቸውና እውቀታቸው በሚዲያ ላይ የራሳቸውን ምስል በአንድ ቤተ ዕምነት የሥርጭት አውታር መሰራጨቱን አውቀውና ያለፈቃዳቸው እንደተሰራጨባቸው ማረጋገጫ ይዘው ከፍርድ ቤት ቢሞግቱ ያለምንም ቅደመ ሁኔታ የሞራል ካሳና በሚዲያውም ላይ እስከ መዘጋት የሚያደርስ ወንጀል መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡

Read 9483 times Last modified on Wednesday, 29 October 2014 06:07
Yoseph Lemma

Email This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

Nahu's Corner

 

 

 

.

Right Now

We have 195 guests and no members online

About Us

Semayawi Thought is an online magazine published in Amharic and English, focused on contents to spiritual and personal growth.