በጥንታዊትነቷ በምትታወቀው በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ብዙ ዘመን ዘለል አባቦሎች እንዳሉ ባውቅም መልዕክቴን ያጎሉልኛል የምላቸውን ላስታውሳችሁ፤ “ለነፍሱ ያደረ ለእግዚአብሔር ኖረ” ….. ‹‹ለሥጋው የኖረ ከመንገድ የቀረ›› ፡፡ ምናልባትም የዚህ ዐይነት አባባሎች ብህትውናን ያስፋፋሉ በመባል በመረሳት ላይ ይገኙ እንጂ ውስጣቸው ያለው ቁም ነገር ዘመን ተሸጋሪ ስለመሆኑ አያከራከርም፡፡
የእኔ ዐይነቱ፡-በሃይማኖት ቤት ውስጥ ያደገ ፤ በተለይም በወንጌላዊያኑ ቤተ እምነት ውስጥ በአዲስና መጤ ትምህርቶች በእውነተኛው የክርስትና ትምህር...