You are here: HomeOpinionsTesfaye Robele
Tesfaye Robele

Tesfaye Robele

ዶክተር ተስፋዬ ሮበሌ በኢንተርናሽናል የመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር የአዲሱ መደበኛ ትርጒም ተርጓሚ ሆኖ ሠርቶአል፡፡ በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የቤተ እምነቱ የሥነ ጽሑፍ ክፍል ኀላፊና የ“ቃለ ሕይወት” መጽሔት ዋና አዘጋጅ ሆኖ አገልግሎአል፡፡ ለዐቅብተ እምነት አገልግሎት ካለው ትልቅ ሸክም የተነሣ፣ ተስፋ ዐቃብያነ ክርስትና ማኅበርን መሥርቶአል፤ በዐቅብተ እምነትም ላይ በርካታ መጻሕፍትን አዘጋጅቶአል፡፡ የዶክትሬት ዲግሪውንም የሠራው ለረጅም ዓመት በሠራበትና ወደ ፊትም በስፋት ሊያገለግልበት በሚፈልገው በክርስቲያናዊ ዐቅብተ እምነት (Christian Apologetics) አገልግሎት ነው፡፡

Website URL: http://www.tesfayerobele.com Email: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
“ቤት ያጣው ቤተኛ” የዚህ ጽሑፍ ፅንሰትና ልደት፣ “የወር ተረኛው” ርእሰ ጒዳይ ነው፡፡ ባልንጀራዬ ዮናስ ጐርፌ፣ “ቤት ያጣው ቤተኛ—ሙዚቃ፣ ሙዚቀኛነትና ኢትዮጵያዊቷ ቤተ ክርስቲያን” በሚል ርእስ ያሳተመው መጽሐፍ እንዲሁም መጽሐፉን ተከትሎ የወጡ በርካታ አጸፋዎችና መወድሶች፣ የዚህ ጽሑፍ መነሻ ናቸው፤ መድረሻ ግን አይደሉም1፡፡ አጸፋዎቹንና መወድሶቹን በተመለከተ ጠቅለል ካለ አስተያየት ያለፈ (ያውም ኢርቱዕ በሆነ መንገድ) ዝርዝር ሐተታ አላቀርብም—ፋይዳ ያለው ስለማይመስለኝ2፡፡ ጌታ ይችን ምስኪን ጽሑፍ ባርኮ ዳርቻዋን ቢያሰፋ ግን፣ ምንኛ ደስተኛ ...
ክርስትና ድሩም ማጉም እምነት ነው፡፡ በእግዚአብሔር ማመን፤ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን፤ በመንፈስ ቅዱስ ማመን፣ በሙታን ትንሣኤ ማመን፣ በክርስቶስ ቤዛዊ ግብር ማመን ወዘተረፈ፡፡ በአጠቃላይ ክርስትና ዋልታና ማገሩ፣ መሠረቱና ውቅሩ እምነት ነው፡፡ የቃሉን ትርጓሜና ዳር ድንበር፣ የመሠረተ ሐሳቡን ስፋትና ጥልቀት እንዲሁም በርእሰ ጒዳዩ ላይ በሚቀርቡ መስመር የሳቱ ትምህርቶችና ልምምዶች ላይ ሒስ መሰንዘር፣ የዚህ ጽሑፍ መነሻም መድረሻም ነው፡፡ በአጭሩ ጽሑፉ ትምህርታዊና ዐቅብተ እምነታዊ ተልእኮ በመሰነቅ፣ ቃለ እግዚአብሔርንና ምክንዩን የጒዞ መስመ...

ክርስትናና ጦርነት

Published in Opinions
Wednesday, 22 April 2015 00:00
በዘመነ ደርግ ሃይማኖት በሕግ ውጉዝ ተግባር ስለነበር፣ሰዎች በሃይማኖታቸው ሰበብ የሚደርስባቸውን ግፍ አቤት የሚሉበት አንዳችም የበላይ አካል አልነበረም፡፡ በዚህ ምክንያት ክርስቲያኖች በመንግሥትም ሆነ በሰፈር ቦዘኔዎች እጅግ ብዙ በደል ሲፈጸምባቸው መቆየቱ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው (ለነገሩ ሃያ ዓመት ዐለፈው እሳ፣ ጊዜ እንዴት ይሮጣል ጃል)፡፡ በዚያ ክፉ ዘመን፣ ክርስቲያኖች ወደ ቤተ አምልኮዎች የሚሄዱት ጨለማን ተገን አድርገው አልያም ሰዎች በብዛት አያዝወትሩባቸውም የሚሏቸውን መንገዶች አሳብረው ነበር፡፡ ከታሪክ ዳኛው ከእግዚአሔር በስተቀር፣ ያገባኛ...
የክቡር ሐዲስ ዓለማየሁን ስመ ጥር መጽሐፍ፣ ፍቅር እስከ መቃብርን በቅጡ ለመረዳት፣ መጽሐፉ የተጻፈበትን የአማርኛ ቋንቋ፣ ትረካው የተዋቀረበትን የታሪክ ዘመን፣ መጽሐፉ በምፀት የሞሞሸልቀውን ሥርዐተ ማኅበር፣ የድርሰቱ ባለቤት የሆነው ሕዝብ የሚጋራውን ባህል፣ የሰሜኑ የአገራችን ሕዝብ የሚኖርበትን መልከዐ ምድር፣ በዘመኑ የነበረውን የቤተ ክህነት ሥርዐትና የነገረ መለኮት አስተሳሰብ እንዲሁም እነዚህ መሰል ጕዳዮች በሚገባ ማወቅ የግድ ይላል፡፡ አልያ ግን ፍቅር እስከ መቃብን አንብቤ በሚገባ ተረድቼዋለሁ ማለት የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ይህን መጽሐፍ እኔ በ...
ማኅበራዊ ግንኙነት ትልቅ ጥንቃቄ የሚሻ ጕዳይ ነው፡፡ በምዕራቡ ዓለም በየደረጃቸው የሚገኙ ማኅበራዊ መስተጋብሮች ደማቅ መስመርና ጠንካራ ዳር ድንበር ስለተበጀላቸው የየግነኙነቶቹ ዳር ድንበሮች በውል ይታወቃሉ፡፡ ክልሎቹን መጣስ ከነውርነት ባለፈም በሕግ ሊያስቀጣ ሲበዛም ዘብጥያ ሊያስወረውር ይችላል፡፡ ከዚህ የተነሣም እነዚህን መከልክሎች ጥሶ የሚሄድ ወፈፌ እንብዛም አይታይም፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ ምዕራባውያን “ግላዊነት” (individualism) በመባል የሚታወቀውን የኑሮ ዘዬ መቀለሳቸው፣ መስመር ስቶ የመጋጨቱ አባዜ በከፍተኛ ቊጥር እንዲቀንስ ምክንያት...

Nahu's Corner

 

 

 

.

Right Now

We have 238 guests and no members online

About Us

Semayawi Thought is an online magazine published in Amharic and English, focused on contents to spiritual and personal growth.