You are here: HomeOpinionsPoetry - ግጥሞችየጭንቅ ቀን ሰው

የጭንቅ ቀን ሰው

Written by  Published in Poetry - ግጥሞች Thursday, 08 May 2014 00:00

ጥርቅምቃሞ ተስፋው ነጥፎ

ከነፍሱ ጭላጭ ተንጠፍጥፎ

ሲነጋ ሲመሽ ተጋድሞ

ስጋው የልቡም ለብ ታሞ

እንዳይሞት ብቻ ኖሮ

በሁለትዮሽ ትብታብ

ታብቶ በመከራ ጥላ ድባብ

ላይቀና ከጋድሚያው ነቅቶ

ላይረግፍ ላያልፍ እሱ ሞቶ

ተራውን በግድ ተቀምቶ

ላይሆንለት ማቅቆ ማቆ

ሰው አጣሁኝ ቅኔውን

የብቻነት በገናውን

አንዝሮ ሰብቆ ክብሩን

አፏጭቶ ተንፍሶ መቃወን

የምሬት እንጉረጉሮ ዜማ

ቀንና ለሊት ሲያሰማ

ያለ ልቅሶ ስራ ቢያጣ

ፀሀይ ጠልቆ እሰኪወጣ

ንጋት ወዲህ እሰኪያገኘው

ሰው የለኝም የሱ ቅኔው

ውሃው ወዲያ ወዲህ ሲሰፍ

በመላዕክት እጅ ሲገረፍ

እግር አጥታ የሱይቱ ነፍሰ

ቀን ሲቀጥር በመከራ

የህይወቱ ነቁጥ ላይጠራ

አዳፋ ነ ፍሱ ላይጸዳ

ምሬት ውስጡን እየላፈው

ቅናት ሰግሮ ሲጋልበው

እኛዎቹ ላዎቹ

ፊት ሲሆኑ  እኩዮቹ

የእረፍቱን ቁልፍ በአይኑ እያየው

እጁን መስደድ ባይቻለው

ከእንባ በቀር ምን ነው ምሱ

ለዚያ ምሰኪን ለዚያች ነፍሱ

ቅኔ ያውጣ ያንጎራጉር

ወይ አልሞተ ውይ ደሞ አይኖር

እንጥፍጣፊ ተስፋ የለው

ቀን ሲቆጥር ዘመን ሸሸው

ሰው የለኝም ውዳሴውን

ሲያነበንብ ያን ድጋሙን

ከሰው ይልቅ የከበረው

ቤዛው መጣ ሊታደገው

ሳይቀዘቅዝ ሳይራጠብ

ከፈውስ ማዕድ እንዲመገብ

ትዕዛዝ ወጣ የሚድነው

ሰው አገኘ ሰው የሌለው

ነፍስ ዘራ የበደነው

የውሃው ዳር ባለዕልፍ ዘመን

ሰው አገኘ የጭንቅ ቀን

 

38 አመት ለተሰቃየው ረዳት አልባ ሰው

Read 16234 times Last modified on Thursday, 08 May 2014 20:34

Nahu's Corner

 

 

 

.

Right Now

We have 153 guests and no members online

About Us

Semayawi Thought is an online magazine published in Amharic and English, focused on contents to spiritual and personal growth.