You are here: HomeNews/Eventsአዲስ ዌቭ- አድሰን! ሙላን! ላከን! ታላቅ የጸሎት እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ

አዲስ ዌቭ- አድሰን! ሙላን! ላከን! ታላቅ የጸሎት እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ

Published in News and Events Friday, 21 August 2015 06:25

የግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ በወንጌል ስርጭት ፣ ደቀ መዛሙርትን  በማፍራት፣ በቤተ ክርስቲያን ተከላና በመሪዎች እድገት ዙሪያ ከአብተ ክርስቲያናት እና መንፈሳዊ ድርጅቶች ጋር ተባብሮ ሲሰራ መቆየቱ ይታወቃል።

 

በግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ ከዛብሎን አገልግሎት ጋር እና ከወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ጋር በመተባበር አዲስ ዌቭ በሚል ስያሜ ከነሐሴ 2007ዓ/ም ጀምሮ ለአስራ ስምንት ወራት የሚዘልቅ ታላቅ የመንፈሳዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ በዝግጀት ላይ እንገኛለን። የዚህ ፕሮግራም አካል እና የመጅመሪያ ምዕራፍ የሆነውን ‘አድሰን’፣’ሙላን’፣’ላከን’ በሚል ትኩረት የተዘጋጀውን ልዩ የጸሎትና የወንጌል ስርጭት እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ ይገኛል።

 

አዲስ ዌቭ ከአማርኛ እና እንግሊዘኛ ቃላት ውህደት የተፈጠረ ቃል ነው ሲሆን በመዲናችን አዲስ አበባ እናም በመላው ኢትዮጵያ እየነፈሰ ያለውን የመንፈሳዊ እንቅስቃሴ ንፋስ የሚያሳይ ስያሜ እንደሆነ ከአዘጋጆቹ ለመረዳት ችለናል። አዲስ የሚለው ጅማሬን ለውጥን የሚያሳይ ሲሆን፣ ዌቭ የሚለው ቃል ደግሞ ሞገድ ወይም እንቅስቃሴን ይወክላል። ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከማረጉ በፊት ደቀመዛሙርቱን እንዲህ ብሎቸዋል። “ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ ።” (ሐዋርያት ስራ 1፡8) ያን ጊዜ የወረደው ይህ የመንፈስ ቅዱስ እሳት በመላው ዓለም ወንጌል ለፍጥረት ሁሉ ይደርስ ዘንድ ብዙዎችን አስነስቷል። ታዲያ አሁን ባለንበት ዘመን ብዙ መንፈሳዊ እና ሌሎች  ችግሮችን እየተመለከትን የመንፈስ ቅዱስን ሙላት በጋራ መጠማትና መናፈቅ ያዳገተን ለምንድን ነው?

 

የሀገራችን ህዝብ ቁጥር ውጤት እንደሚያሳየው 60% የሚሆነው ህዝብ ዕድሜው ከ35 በታች ነው። በሁሉም ዘርፍ ብርቱ የለውጥ ኃይል የሆነው ወጣቱ ሲሆን ክርስቲያን ወጣቶች ደግሞ በቤ/ክርስቲያንም ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛሉ።  ነገር ግን ፈርጀ ብዙ የሆኑ ተግዳሮቶችና ፈተናዎች ወጣቶቹ ለተጠሩለት የክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ መኖር እንዳይችሉ እንቅፋት ሆነውባቸዋል፡፡ ለአብነት ያህል፣ የአቻ ግፊት፣ ድኅረ-ዘመናዊነት፣ በሱሶች መጠመድ፣ ውርጃ፣ የስህተት ትምህርቶች መበራከት ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ከዚህም የተነሳ፣ ዛሬ ዛሬ፣ በጠቅላላው ህዝበ ክርስቲያን በተለይም በወጣቶቹ ዘንድ በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ ሕይወትን መኖር ጊዜው ያለፈበት ነገር እየመሰለ መጥቷል፡፡

 

በሌላ በኩል ደግሞ መሪዎች እናቶች እና አባቶች ብሎም ወጣቶች በምድራችን እግዚአብሔር የወንጌል እሳት እንደገና እንዲቀሳቀስ እይፀለዩ ይገኛሉ። አዲስ ዌቭ ጅማሬውን “አድሰን ሙላን ላከን” በሚል መርህ  ታጅቦ በፀሎት እንቅስቃሴ ለመጀመር የተነሳው ለዚህ ነው።

  

የጸሎቱም መርሃግብር ከነሐሴ 22 እስከ ጳጉሜ 1፥ 2007 ዓ.ም እንደሚሆንና ጸሎቱ የሚካሄድበትን ቦታዎች ከታች እንዲመለከቱ እናሳስባለን።

 

Semayawi Thought የዚህ ዌቭ አካል እንዲሆኑም ይጋብዛል።

 

ቀንሰዓትፕሮግራም
አርብ ነሐሴ 22 ከምሽቱ 11:30 – 2፡00 አዲስ ዌቭ የመክፈቻ ፕሮግራም
በ10 ክፍለ ከተማዎች የተመረጡ የፀሎት ማዕከላት
ቅዳሜ ነሐሴ 23 ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ
ሙሉ ቀን
የፀሎት አመራር ኮንፍራንስ
ዕሁድ ነሐሴ 24 ከከሰዓት 7:00 – 11:00 የፀሎት አመራር ቀጣይ ስልጠና እና ማጠቃለያ
ሰኞ ነሐሴ 25 ከጠዋቱ 1:00 – 7:00 የፆም ፀሎት ፕሮግራም
ከምሽቱ 11:30 – 2፡00 የመነቃቂያ ኮንፍራንስ
መሪ ሀሣብ – አድሰን
ማክሰኞ ነሐሴ 26 ከጠዋቱ 1:00 – 7:00 የፆም ፀሎት ፕሮግራም
ከምሽቱ 11:30 – 2፡00 የመነቃቂያ ኮንፍራንስ
መሪ ሀሣብ – አድሰን
ዕሮብ ነሐሴ 27 ከጠዋቱ 1፡00 – 9፡00 የፆም ፀሎት ፕሮግራም
የእግር ጉዞ ፀሎት በፀሎት ማዕከላት አካባቢ
ከምሽቱ 11:30 – 2፡00 የመነቃቂያ ኮንፍራንስ
መሪ ሀሣብ – ሙላን
ሐሙስ ነሐሴ 28 ከጠዋቱ 1፡00 – 9፡00 የፆም ፀሎት ፕሮግራም
የእግር ጉዞ ፀሎት በፀሎት ማዕከላት አካባቢ
ከምሽቱ 11:30 – 2፡00 የመነቃቂያ ኮንፍራንስ
መሪ ሀሣብ – ሙላን
አርብ ነሐሴ 29 ከጠዋቱ 1:00 – 9፡00 የፆም ፀሎት ፕሮግራም
የእግር ጉዞ ፀሎት በፀሎት ማዕከላት አካባቢ
ከምሽቱ 11:30 – 2፡00 የመነቃቂያ ኮንፍራንስ
መሪ ሀሣብ – ላከን
ቅዳሜ ነሐሴ 30 ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ
ሙሉ ቀን
የጋራ የአንድነት የፀሎት እና የመነቃቂያ ኮንፍራንስ
በቦሌ ምስራቅ መሰረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን
ዕሁድ ጳጉሜ 1 ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ የጋራ የአንድነት የፀሎት እና የመነቃቂያ ኮንፍራንስ
በቦሌ ምስራቅ መሰረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን
Read 6369 times Last modified on Friday, 21 August 2015 07:05

Nahu's Corner

 

 

 

.

Right Now

We have 135 guests and no members online

About Us

Semayawi Thought is an online magazine published in Amharic and English, focused on contents to spiritual and personal growth.