You are here: HomeNews/EventsTurning Point በሚል ርዕስ በአይነቱ ልዩ የሆነ የወጣቶች ፕሮግራም ተዘጋጅቶአል።

Turning Point በሚል ርዕስ በአይነቱ ልዩ የሆነ የወጣቶች ፕሮግራም ተዘጋጅቶአል።

Published in News and Events Monday, 10 August 2015 06:19

የፊታችን ነሐሴ 17  እሁድ ከ 8 ሰዓት ጀምሮ Turning Point  በሚል ርዕስ በባይብል አርሚ - ኪንግደም አጥቢያ (ባምቢስ አካባቢ በሚገኘው) በአይነቱ ልዩ የሆነ የወጣቶች ፕሮግራም ተዘጋጅቶአል ፡፡ ለፕሮግራሙ የተሰጠው ስያሜ እና እየተደረገ ያለው ዝግጅት ከተለመደው ወጣ እንደሚል የፕሮግራሙ አዘጋጆች የገለጹልን ሲሆን ይህ ፕሮግራም በየመፅሐፍ ቅዱስ ሠራዊት ዓለም ዐቀፍ ቤተክርስቲያን - የወጣቶች አገልግሎት እና ጋፕስ ዓለም ዐቀፍ ሚኒስትሪ በመተባበር የተዘጋጀ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል። ፕሮግራሙ ወጣቶችን በወንጌል ለመድረስ ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን ከዕለቱ በፊት በከተማዋ ዋና ዋና ቦታዎች የአንድ ለአንድ እና ዲጂታል የወንጌል ስርጭት ይደረጋል።

 

በዕለቱ የእግዚአብሔር ቃል በቶማስ ምትኩ የሚቀርብ ሲሆን ዘማሪ አይዳ ከለንደን፣ዘማሪ ይስሐቅ ፣የቤዛ ቸርች መዘምራን ፣የባይብል አርሚ መዘምራን እና ጆ-ቲም ወጣቶች መዘምራን እንዲሁም ኬሮግራፊ እና የተለያዩ ዝግጅቶች ይቀርባሉ ፡፡

 

ፕሮግራሙ ነሐሴ 17 በአዲስ አበባ ከተደረገ በኋላ በቀጣይ በሌሎች ከተሞች እና ብሎም ከሐገር ውጭ በተለያዩ ስፍራዎች ለማድረግ እነደታቀደ ገልፀውልናል ፡፡

 

በመጨረሻም አዘጋጆቹ አማኞች በዚህ ፕሮግራም ላይ የሚያውቀቸውን ሁሉ በመጋበዝ እንደዲገኙ እና በፌስቡክ እና ሌሎች ማህበራዊ ደህረገፆች ላይ በማስተዋወቅ አብራችሁን ቁሙ በማለት መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ ፡፡

 

ለዚህ ፕሮግራም በሚደረገው የወንጌል ስርጭት ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ 2519 11 485782  በመደወል ማነጋገር ይችላሉ

Read 6009 times Last modified on Monday, 10 August 2015 06:30

Nahu's Corner

 

 

 

.

Right Now

We have 267 guests and no members online

About Us

Semayawi Thought is an online magazine published in Amharic and English, focused on contents to spiritual and personal growth.