የፊታችን ነሐሴ 17 እሁድ ከ 8 ሰዓት ጀምሮ Turning Point በሚል ርዕስ በባይብል አርሚ - ኪንግደም አጥቢያ (ባምቢስ አካባቢ በሚገኘው) በአይነቱ ልዩ የሆነ የወጣቶች ፕሮግራም ተዘጋጅቶአል ፡፡ ለፕሮግራሙ የተሰጠው ስያሜ እና እየተደረገ ያለው ዝግጅት ከተለመደው ወጣ እንደሚል የፕሮግራሙ አዘጋጆች የገለጹልን ሲሆን ይህ ፕሮግራም በየመፅሐፍ ቅዱስ ሠራዊት ዓለም ዐቀፍ ቤተክርስቲያን - የወጣቶች አገልግሎት እና ጋፕስ ዓለም ዐቀፍ ሚኒስትሪ በመተባበር የተዘጋጀ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል። ፕሮግራሙ ወጣቶችን በወንጌል ለመድረስ ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን ከዕለቱ በፊት በከተማዋ ዋና ዋና ቦታዎች የአንድ ለአንድ እና ዲጂታል የወንጌል ስርጭት ይደረጋል።
በዕለቱ የእግዚአብሔር ቃል በቶማስ ምትኩ የሚቀርብ ሲሆን ዘማሪ አይዳ ከለንደን፣ዘማሪ ይስሐቅ ፣የቤዛ ቸርች መዘምራን ፣የባይብል አርሚ መዘምራን እና ጆ-ቲም ወጣቶች መዘምራን እንዲሁም ኬሮግራፊ እና የተለያዩ ዝግጅቶች ይቀርባሉ ፡፡
ፕሮግራሙ ነሐሴ 17 በአዲስ አበባ ከተደረገ በኋላ በቀጣይ በሌሎች ከተሞች እና ብሎም ከሐገር ውጭ በተለያዩ ስፍራዎች ለማድረግ እነደታቀደ ገልፀውልናል ፡፡
በመጨረሻም አዘጋጆቹ አማኞች በዚህ ፕሮግራም ላይ የሚያውቀቸውን ሁሉ በመጋበዝ እንደዲገኙ እና በፌስቡክ እና ሌሎች ማህበራዊ ደህረገፆች ላይ በማስተዋወቅ አብራችሁን ቁሙ በማለት መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ ፡፡
ለዚህ ፕሮግራም በሚደረገው የወንጌል ስርጭት ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ 2519 11 485782 በመደወል ማነጋገር ይችላሉ