You are here: HomeNews/Eventsበወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ያሉ አሳሳቢ ጉዳዮች ላይ የሚመክር አውደ ጥናት ነገ ይጀምራል።

በወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ያሉ አሳሳቢ ጉዳዮች ላይ የሚመክር አውደ ጥናት ነገ ይጀምራል።

Published in News and Events Thursday, 11 June 2015 00:00

በወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ያሉ አሳሳቢ ጉዳዮች ላይ የሚመክር አውደ ጥናት እና የምክክር መድረክ ነገ ከሰኔ 5 እና 6 2007 ዓ.ም. በአቫንጀሊካል ቲዮሎጂካል ኮሌጅ ይጀምራል።

 

በኢትዮጵያ የሚገኙ የወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት በእግዚአብሔር ጸጋና ርዳታ እግዚአብሔርን መንግሥት የማስፋፋት ተግባራትን እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡ ሆኖም አሁን በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለው ተጨባጭ ሁኔታ ሲመዘን በምድሪቱ ላይ በጎ ተጽዕኖ ለማሳደር እንዳይቻል እና የእግዚአብሔር ስም እንዲሰደብ የሚያደርጉ አሳሳቢ ጉዳዮች መኖራቸው ግልጽነው፡፡ በዚህም ምክንያት ታሪካዊና አስፈላጊ የሆነ ዐውደ ጥናት እና የምክክር መድረክ ተዘጋጅቷል፡፡

 

ይህ ታሪካዊና አስፈላጊ የሆነ ዐውደ ጥናት እና የምክክር መድረክ እጅግ አሳሳቢ በሆኑ ጉዳይ ላይ በመመካከርና በመጸለይ በቆዩ ወገኖች አነሳሽነት የቤተክርስቲያን አጋዥ በሆኑ ተቋማት ማለትም ቢብሊካ ኢትዮጵያ፣ የወንጌላውያን ዮንቨርሲቲ ተማሪዎችና ምሩቃን ማኅበር (ኢቫሱ)፣ ደወል የወንጌል አገልግሎት፣ ቃለ እግዚአብሔር አንባቢያን ማኅበር፣ ጎልደን ኦይል አገልግሎት፣ እና ኢቫንጀሊካል ቲዮሎጂካል ኮሌጅ አስተባባሪነት የተዘጋጀ ሲሆን ሸክሙን ለመሪዎችና ለአገልጋዮች ለማካፈል እንዲሁም የተሐድሶ እንቅስቃሴ ለመፍጠር የሚያስችል የምክክር መድረክ ነው፡፡

 

ዐውደ ጥናቱ እና የምክክር መድረኩ በዋነኛነት “የሕይወት ጥራት”፣ “የአስተምህሮ ጥራት”፣ እና “የአመራር ጥራት” በሚሉ ርዕሶች ላይ የሚያተኩር ሲሆን ለውይይት መነሻ የሚሆኑ ጽሑፎችም ተዘጋጅተዋል፡፡

 

በዚህ ዐውደ ጥናት እና የምክክር መድረክ ከ500 በላይ የሚሆኑ መሪዎች የሚገኙበት ሲሆን ከመወያየት ባሻገር የተለያዩ ተግባራዊ እርምጃዎች እና አገር አቀፍ የመንፈሳዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ ለማስጀመር ትልቅ እድል የሚፈጠርበት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

 

Semayawi Thought ዝግጅቱን እንደሚዘግብና ለአንባቢዎች እንደሚያቀርብ ከወዲሁ ያስታውቃል። 

Read 5456 times Last modified on Thursday, 11 June 2015 13:34

Nahu's Corner

 

 

 

.

Right Now

We have 262 guests and no members online

About Us

Semayawi Thought is an online magazine published in Amharic and English, focused on contents to spiritual and personal growth.