You are here: HomeNews/Eventsኢትሲ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የድህረ ምረቃ ፕሮግራም ያጠናቀቁ ተማሪዎችን አስመረቀ

ኢትሲ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የድህረ ምረቃ ፕሮግራም ያጠናቀቁ ተማሪዎችን አስመረቀ

Published in News and Events Monday, 08 June 2015 00:00

ኢቫንጀሊካል ቲዎሎጂካል ኮሌጅ ባለፈው ሳምንት ለ 27ኛ ጊዜ የ2007 ዓ.ም. ተማሪዎችን አስመረቀ። በእለቱ የኮሌጁ ፕሪንሲፓል ዶ/ር ስምኦን ሙላቱ ቤተክርስቲያን በስደት ውስጥና እንዲሁም በፍጥነት በማደግ ላይ በነበረችበት ጊዜ ለመጪው ዘመን ቤተክርስቲያንን የሚያገለግሉ በመጽሐፍቅዱስ፣ በነገረ-መለኮትና በአገልግሎት ክህሎት የተዘጋጁ አገልጋዮችን የማፍራት ራዕይ በነበራቸው ሰዎች አነሳሽነት ከ 32 አመታት በፊት 1975ዓ.ም. መመስረቱን አስታውሰው ያኔ ትምህርቱ የጀመረው ከ 11 አብያተክርስቲያናት በመጡ 17 ተማሪዎች እንደነበርና በእግዚአብሔር እርዳታ ኢቲሲ ለወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት በሩን ክፍት አድርጎ አገልጋዮችን ሲያሰለጥን እንደቆየ ገልጸዋል።

 

የኢቲሲ ተመራቂዎች ጌታንና ቤተክርስቲያንን በተለያዩ አብያተክርስቲያናት የአገራችን ክፍሎችና ከአገራችን ዉጪ በተለያዩ አገሮች እያገለገሉ እንደሚገኙና በዛን እለት የተመረቁት ተማሪዎች እስከ ዛሬ ከሶስቱ ፕሮግራሞቻችን የተመረቁትን ተማሪዎች ቁጥር ወደ 1,072 ያደርሰዋል ብለዋል።

 

የእለቱን የምረቃ በአል እስከ ዛሬ ከነበሩን ምረቃዎች ሁሉ ልዩ የሚያደርገው ኢትሲ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የድህ ረምረቃ ፕሮግራም ያጠናቀቁ ተማሪዎችን ማስመረቁ ነው።እነዚህ ተማሪዎች ኢቲሲ ከጀመራቸው ሁለት የማስተርስ ፕሮግራሞች አንዱ በሆነው ሆሊስቲክ ቻይልድ ዴቬሎፕመንት ነው። በእለቱም የተመረቁት 78 ተማሪዎች ሲሆኑ 3 ዲፐሎማ ኦፈ ቲኦሎጂ መርሃግብር 4 አሶሲየት ኦፈ ቲኦሎጂ ዲግሪ መርሃ ግብር እና 52 በባችለር ኦፍ ትዮሎጅ ዲግሪ መርሃ ግብር ተመርቀዋል።

 

የ ኢቲሲ ኮሌጅ አገልግሎቱንም በማስፋት ከሁለት አመት በፊት የኤክስቴንሽን ፕሮግራም በሃዋሳ ከተማ መጀመሩ ይታወቃል። ይህም አዲስ አበባ መጥተው በሙሉ ጊዜ ትምህርታቸውን መከታተል ለማይችሉት ተማሪዎች ትልቅ እድል ሰጥቶአል።ከዚህም በተጨማሪ አገልግሎታቸውንና ቤተሰባቸውን ትተው አዲስ አበባ ለመምጣት የማይችሉ ኢቲሲ ግን ገብተው ለመማር የሚፈልጉ ብዙ ሰዎች እንዳሉ በመገንዘብ የኢቲሲን ፕሮግራሞች በገና እረፍትና በክረምት ብቻ ሊከታተሉ የሚችሉበትንም መንገድ በማመቻቸት ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ችለናል።

 

በእለቱም ዶ/ር ስምኦን ለምንጨምራቸው አዳዲስ ፕሮገራሞች በቂ ቦታ እንዲኖረን በማሰብ በሜክሲኮ አካባቢ ጌታ በሰጠን መሬት ላይ ባለ ፩፫ ፎቅ አዲስ ሕንጻ ለመስራት ዝግጅታችንን አጠናቀናል ብለዋል። ለዚህም ሕንጻ ግንባታ የሚሆን ገንዘብ ለማሰባሰብ የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ እንደሚገኙና ለዚህ ሁሉ የአብያተክርስቲያናትን ጸሎትና ድጋፍ እንዳይለየን ሲሉ አደራ ብለዋል።

 

ተማሪዎችን በመላክ፣ የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ በመስጠት ለአገልግሎታቸው መሳካት በመጸለይና በመደገፍ የተባበሩትን  ሁሉ በዚህ አጋጣሚ አመስግነዋል።

Read 5549 times

Nahu's Corner

 

 

 

.

Right Now

We have 148 guests and no members online

About Us

Semayawi Thought is an online magazine published in Amharic and English, focused on contents to spiritual and personal growth.