You are here: HomeNews/Eventsኑ ወደ ኢተዮጲያ እንሂድ

ኑ ወደ ኢተዮጲያ እንሂድ

Published in News and Events Wednesday, 17 June 2015 00:00

በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ አለም አቀፍ የወጣቶች መንፈሳዊ እንቅስቃሴ በኢትጲያ ተጀምሯል። ብሌዝ ሙቭመንት (Blaze movement) በመባል የተሰየመመው ይህ እንቅስቃሴ በምድራችን ላይ መንፈሳዊ ተሃድሶን ለማምጣት ታስቦ የተመሰረተ ነው። ይህም መንፈሳዊ ተሃድሶ በኛ ዘመን ይሆናል ብለን እናምናለን በማለት የእንቅስቃሴው መስራቾች ይናገራሉ፡፡

 

ብሌዝ ማለት የሚቀጣጠል እሳት ማለት ሲሆን በወንጌል የሚቃጠሉ ወጣቶችን ለማፍራት ትልቅ ራዕይን ሰንቋል። እንደሚታወቀው ከግማሽ በላይ የሚሆነው የኢተዮጲያ ሕዝብ ወጣት ነው ይሁን እንጂ አብዛኛው ወጣት በተለያየ ነገር ተጠምዶ ይገኛል፡፡ 

 

ብሌዝ አለም አቀፍ የወጣቶች መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ከማንኛውም መንፈሳዊና ስጋዊ እስራት የተፈቱ ወጣቶች በመንፈስ እየተቀጣጠሉ ለእግዚአብሔር መንግስት ሲተጉ ማየትን ራዕይ አድርጎ እንደተነሳና ከሰኔ 18 እስከ ሃምሌ 18/2007 ዓ.ም በሚቆየው የመጀመሪያው እንቅስቃሴ በርካታ ኘሮግራሞችን በውስጡ እንዳካተተ ከነዚህም መካከል የተለያዩ መንፈሳዊ ኘሮግራሞች ፀሎት፣ ወንጌል ስርጭት ፣ ትምህርቶችና ስልጠናዎች ፣ ምስክትነቶች ከተለያዩ አገር ከሚመጡ የወጣቶች አገልግሎት የሚደረግ የልምድ ልውውጥ በተጨማሪም የተለያዩ የበጐ አድራጎት ስራዎች ከነዚህም መካከል ከተማን ማፀዳት ፣ ችግረኞችን መጐብኘት ከዚህም በተጨማሪ የተለያዩ ለወጣቶች የሚሆኑ ጨዋታዎች ውድድሮችንም በውስጡ ማካተታቸውን የኘሮግራሙ አዘጋጆች ነግረውናል፡፡

 

ይህም የአንድ ወር የኘሮግራም በወሩ መጨረሸ በሚደረግ የወጣቶች ኮንፈረንስ የሚጠናቀቅ ይሆናል።  በዚህም ኘሮግራም ላይ ለመሳተፍ አያሌ ሰዎች ከተለያዩ አለማት መምጣት ጀምረዋል። ተራው የእርሶዎ ነው በማለት የኘሮግራም አዘጋጆች ጥሪያቸውን ያቀርባሉ፡፡

 

ለበለጠ መረጃ www.blazemovement.com 

Read 5980 times Last modified on Wednesday, 17 June 2015 05:26

Nahu's Corner

 

 

 

.

Right Now

We have 221 guests and no members online

About Us

Semayawi Thought is an online magazine published in Amharic and English, focused on contents to spiritual and personal growth.