You are here: Home

መልሰኝ ወደ መጀመሪያው መልሰኝ ወደ ቀድሞ ህይወቴ

Published in Video Monday, 20 July 2015 07:36

መልሰኝ ወደ መጀመሪያው መልሰኝ ወደ ቀድሞ ህይወቴ

መልሰኝ ወደ ዳንኩበት ቀን መልሰኝ ወደ ቅንነቴ

 

ለሚመታኝ  ያለ ምክንያት ስባርከው ያለመሳሳት

ቀኜን ለሚመታኝ ግራዬን እንዲገርፈኝ ስሰጥ አካሌን

ግን አሁን እንኳን እንዲህ ላደርግ የተናገረኝንም አልለቅ

ያ የዋህነቱ ጠፍቶብኝ ግልፍ ግልፍ ነው የሚያደርገኝ

ወደ ቀድሞው ልመለስ እንጂ ኧረ ይሄ እኮ ጤናም አይደል

አካሄዴን አርመው ጌታ ጉዞዬ እንዳይሆን ወደ ገደል

 

መልሰኝ ወደ መጀመሪያው...

 

ያኔ ድሮ ያኔ ገና ወደ ቤትህ ስመጣ ጌታ

የነበረኝ የህይወት ውሳኔ አልረሳውም ያንን ትልቅ ወኔ

ያደረግህልኝ ሲነግሩኝ እንዴት እንዳዳንከኝ ሲሰብኩኝ

ውስጤ የገባው የፍቅርህ እሳት ሳላቀጣጥል አከሰምኩዋት

ያወቅሁ መስለሆኝ ሁሉም የገባኝ ክርስትናን ኖሬ የጨረስኩኝ

እንደ ቀለም ትመህርት ገስግሼ የተመረቅሁ መስሎኝ ጨርሼ

ለካ ምሩቅ የለም አንተ ጋ በዚህች ዓለም ሳይከፍል ዋጋ

እለት እለት መስቀል ተሸክሞ ስጋን በጥርስ ንክስ አድርጎ

የሚያስችለውን ጸጋን ደርቦ

በጽድቅ ተሻግሮ ያመለጠ እሱ ነው ጨርሶ የተመረቀ

ይህንን ዓለም አልፎ ያመለጠ እርሱ ነው ጨርሶ የተመረቀ

 

መልሰኝ ወደ መጀመሪያው...

 

ያኔ ድሮ ኃጢአት ማለት ለኔ ኃጢአት ነው ሌላ ትርጉም የለው

ያኔ ድሮ ዝሙት ማለት ለኔ ዝሙት ነው ሌላ ትርጉም የለው

ያኔ ድሮ ዘፈን ማለት ለኔ ዘፈን ነው ሌላ ትርጉም የለው

ያኔ ድሮ ውሸት ማለት ለኔ ውሸት ነው ሌላ ትርጉም የለው

አላመቻምችም ጥቅስ አላበዛለት እንደዚያው እንዳለ እንደተጻፈለት

ነበር የማምንበት

ዛሬ ግን ስደምር  አንዳንዴ ስቀንስ

ለራሴ እንዲመቸኝ ስሰርዝ ስደልዝ

ማድረግ አልቻልኩ እንጂ ለኔ እንደሚስማማ

ሌላ መጽሐፍ ቅዱስ ባሳትም አልጠላ

 

አቤት ውድቀት ውድቀት

አቤት ውድቀት ከውድቀትም ውድቀት

አውጣኝ በምህረትህ ልዳን ባንተ እውቀት

መልሰኝ ወደ መጀመሪያው....

 

በመጀመሪያ የፈሰሰው በልቤ ያንተ ፍቅር ነው

ከዚያ ሁሉን ሰው መውደድ ጀመርኩ ጥላቻን ከልቤ አባረርኩ

የነፍሳት ፍቅር በውስጤ ገባ ሰው ወደ ሲኦል እንዳይገባ

ሳነባ ሳነባ መሽቶ እስኪነጋ

ሳነባ ትዝ ይለኛል ሳነባ መሽቶ እስኪነጋ

 

ተቀጣጥሎ የወንጌል እሳት ይሉኝታን ረግጬ ጥያት

ቢሰድቡን ቢንቁኝ ግድ የለኝ ውስጤ የገባው እውነት አያስችለኝ

የሚጠሉኝን ስወዳቸው ቢያባርሩኝም ናፍቂያቸው

ተመልሼ ሄድኩኝ ቤታቸው ወንጌሉን ልነግራቸው

 

አይ ቅንነት የዋህነት ዛሬስ ቢኖረኝ ምን አለበት

የቆምኩ መስሎኝ ለካ ወድቄአለሁ ያንተን ርዳታ እሻለሁ

 

በመንፈስህ ሃይል ስትሞላኝ በቋንቋም ስታናግረኝ

ቀኑን ሙሉ ውዬ ሌሊት ባድር አልረካም በጸሎት ፍቅር

ማለቂያ የለው የጸሎት ርእሴ ባቀርብ ምስጋናን ውዳሴ

ስጸልይ ስተጋ እስከሚነጋ

ስጸልይ ትዝይለኛል ስተጋ እስከሚነጋ

 

ተራራን የሚንድ እምነቴ ግንቡ ሲፈርስ በጩኸቴ

በውስጤ ኃይልህ የኔ ጌታ ሲያራምደኝ በከፍታ

ለኃጢአት የማይታለል ለበረኝ ልብ ከቶ የማይዝል

ሁሌ የነቃ የጨከነ ለቃልህ ሞኝ የሆነ

 

አይ ቅንነት የዋህነት ዛሬስ ቢኖረኝ ምን አለበት

የቆምኩ መስሎኝ ለካ ወድቄአለሁ ያንተን ርዳታ እሻለሁ

መልሰኝ ወደ መጀመሪያው....

Read 7603 times

Most Read

ከእግዚአብሔር ጋር የሚሠራ...

Written bySolomon Abebe Gebremedhin

It is Okay not t...

Written byMeskerem T. Kifetew, PharmD

Lust On a Driver...

Written byMeskerem T. Kifetew, PharmD

የአገር ያለህ!...

Written byNegussie Bulcha

 

 

 

.

Right Now

We have 230 guests and no members online

About Us

Semayawi Thought is an online magazine published in Amharic and English, focused on contents to spiritual and personal growth.