21ኛው ክፍለ-ዘመን በኮምፒውተር ቴክኖሎጂ አለማችን የናኘችበት ዘመን ነው። በዚህ ቴክኖሎጂ የሚሠሩትን-በተራ ሰው አዕምሮ መገመትና ማወቅ አይቻልም። ነገር ግን አብዛኞቻችንን ከኮምፒውተር ጋር ያስተዋወቀ አንድ ግኝት ይዞ መጥቷል:- ፌስቡክ። ድሮ ኮምፒውተርን እንደ ጦር የምንፈራ ሰዎች-አሁን እድሜ ለፌስቡክ እንኳን ልንፈራው፤ ውሏችን ከእርሱ ጋር ሆኗል። ኧረ አንዳንዴም በውሎ ብቻ ካለፈ መልካም ነው-አዳርም እኮ አለ!! ይህንን በማለቴ አላግባብ የሆነ የፌስቡክ አጠቃቀምን ማበረታቴ እንዳልሆነ መቼስ ማስረዳት ያለብኝ አይመስለኝም-እንኳንና ተበረታተን እን...