ዘለቃ(ቃቁ) በቀለ መርሻ እባላለሁ። በአሁን ጊዜ አሜሪካን በሜሪላንድ ሲለቨር ስፕሪንግ ከባለቤቴ ጋር እኖራለሁ። በትዳር አርባ አንድ አመት አሳልፍናል። የአራት ልጆች እናት እና የአምስት የልጅ ልጆች አያት ነኝ። ቤተሰብን በማማከር ከሰላሣ አመት በላይ ጌታን አገልግያለሁ አሁንም በትዳር ውድቀታችንም ሆነ መነሳታችንን ለሚቀጥለው ትውልድ በማካፈል ያገቡትንም ሆነ ያላገቡትን ሕይወታችንን እናካፍላለን። በጁን 2013 "ትዳር ሲቃኝ" የተባለ መጽሐፍ ከባለቤቴ ከኮ/ል ክፍሌ ሥዩም ጋር ጽፈናል። የ"ትዳር ሲቃኝ የቤተሰብ አገልግሎት" በ2014 ዓመት ምሕረት የቲቪ. አገልግሎትም ጀምረናል።
.