እሹሩሩ ሥጋ - ታዘል በጀርባዬ
አንተን ተሸክሜ
ብትቆስልም ነፍሴ-ቢዝልም መንፈሴ
እሹሩሩ ሥጋ - ታዘል በጀርባዬ
ሲከፋህ አልወድም
ፅድቄም ቢወላገድ-ቢገታ እርምጃዬ
የነፍሴ ቅኔዋ-እንደዚህ ሆኖባት
ጠላትዋን ባንቀልባ - እሹሩሩ ማለት
ታማ ተገኝታለች
እየሰሩ ማፍረስ- ከሰልፍ አስፈግፍጓት
እሹሩሩ ሥጋ - ታዘል በጀርባዬ
አንተን ተሸክሜ
ብትቆስልም ነፍሴ-ቢዝልም መንፈሴ
እሹሩሩ ሥጋ - ታዘል በጀርባዬ
ሲከፋህ አልወድም
ፅድቄም ቢወላገድ-ቢገታ እርምጃዬ
የነፍሴ ቅኔዋ-እንደዚህ ሆኖባት
ጠላትዋን ባንቀልባ - እሹሩሩ ማለት
ታማ ተገኝታለች
እየሰሩ ማፍረስ- ከሰልፍ አስፈግፍጓት
Hermela Solomon is passionate about God and the Arts. She has written continuous articles on Addis Admas, worked at Whiz Kids Workshop (tsehay memar twedalech) and contributed 3 books as part of the package to encourage Early Graders reading.
.