እኔ - እርግጠኛ ነኝ ፍቅሩ እንደማይተወኝ
እወድሻለሁ የሚለው ከልቡ እንደሆነ ዐውቃለሁ፡፡
የፈተንኩት መውደዱ ጥርጥሬን አስትቶኛል፡፡
እፎይ ብዬ እኖራለሁ ... ያ ፈ ቅ ረ ኛ ል፡፡
እሱም - ለሱ ፍቅር እንዳለኝ ያስባል
እወድሃለሁ ስለው እንዳ’ፌ ተስፋ ያ’ረጋል::
ያነጠረው መውደዴ ግን የሚጣል ይበዛበታል
ከሚዛን ሁሌ ይጎድላል፡፡
በፍቅሩ ልወቀስ እንጂ ቢሠጋኝ አልፈርድበትም
በ“እወድሀለሁ” መሃላ አልገበዝም፡፡
ባለፈው እንዲያ ባልኩ ማግስት
ብየዋለሁ አላውቅህም፡፡
ዝም ልበል .... አሁን ግን ዝም፡፡
ማረፊያ መንግስት 4/8/10