"ከሀጢያት በስተቀር የቀረብን የለም
ዛሬም አለም ተስፋ ቁረጭ አልተገናኘንም!"
ሙሉቀን መለሰ
ባሳለፍነው እሁድ EBS በእንጨዋወት ፕሮግራሙ የጥንቱን ድንቅ ድምፃዊ ጋሽ ሙሉቀን መለሰን ቃለመጠየቅ ለእይታ ካበቃ በኋላ ከፊል ዘመን ባላደበዛዛቸው ዘፈኖቹ በትዝታ ሲወዘውዝ ገሚሱ ከአመታት በፊት ያስደመጠውን የዝማሬ ሰንዱቅ ከሸጎጠበት ፈልጎ እያዳመጠ በትውስታ ግርሻ ስሙን እያነሳሳ ነው::
አድናቆት እና ትችት ሀዘኔታና ፍርድ እየተግተለትለ የተለመደው የድረ-ገፅ ምልልስ ላይ የአንዳንድ ግለሰቦች ነቆራና አስተያየት የሚያሸማቅቅ...