አጃቢ የሚያጋብስ - ታምር ባይሰራ
እጅን ባፍ የሚያስጭን - ለመነጋገሪያ
ከወትሮ ወጣ ያለ - ቀልብን የሚከትር
አዲስ የተሰኘ - ምንም ነገር ባይኖር
ያ´ዕዋፍ ምስጋና - የሰማይ ዳመና
የቀኑ መንጋቱ - የማለም ውበቱ
የወዳጅ ፈገግታ - የእስትንፋስ ስጦታ
ጀንበር ዝቅዝቅታዋ - ጨረቃም መውጣቷ
ጤና መለምለሙ - ከሰርክ መታደሙ
የህይወት ዑደቱ
የተዘራው ታጭዶ - ዳግም መዘራቱ
ተለምዶ አድርገሽው ባ´ይንሽ ፊት አይቅለል
ያልተገኘ ለታ
ውሃም ዕንቁ ይሆናል
ውሃም ዕንቁ ያስንቃል!!!