ዘፈንና ዘፋኝነትን ጤናማ ድርጊት አድርገው ሊወስዷቸው የሚፈልጉ ክርስቲያኖች አንዳንድ ማመቻመቺያ ሃሳቦችን ሊመዝዙ ይዳዳቸዋል። አንዳንዶች “ዳዊትም እኮ ዘፍኗል።” ይላሉ። ሌሎች ደግሞ “እግዚአብሔርን በዘፈን አመስግኑት ተብሎ ተጽፏል” ይላሉ። አንዳንዶች ደግሞ “መኃልየ መኃልይ ዘሰለሞን በሙሉ ስለወንድና ሴት ፍቅር ነው የሚያወራው እኛስ ተቃራኒ ጾታን እያደነቅን ብናንጎራጉር ምን ይለናል - ፍቅርንስ የፈጠረው እሱ አምላክ አይደል” ብለው ዘፋኝነትነትን ላለመልቀቅ ምክንያታዊ ጥያቄ ያቀርባሉ።
በዘፈንና በዝማሬ መካከል ብዙም ልዩነት እንደሌለ አድር...