ያደባባይ ድምቀት
የመድረክ ላይ ጩኸት
ሲሆንልኝ ሙቀት፧
ጋቢዬን ደርቤ
በሠው ተከብቤ
በጩኸት ታጅቤ
ከወግ ሥርዓቱ
ከባህል ሂደቱ
ተምሬ አሣምሬ
በወጉ ታስሬ
በቤቱ መቀመጥ
መስሎኝ ወንበር ማሞቅ
አደገች ሚያስብለኝ
የሚያስመሰግነኝ
ሣላነብ ሠምቼ
ሚሉትን አውርቼ
ባልታከመ ሚዛን
ክብደትን ደፍቼ
የነኩህን ነክቼ
ሊመሽ ነው መሰለኝ
ቀኑ ጠቆረብኝ
አንተንም ሣልነካ
እኔም ሣልነካ