You are here: HomeNews/Eventsቲቢ ጆሽዋ ታንዛኒያ መግባታቸው ተነገረ

ቲቢ ጆሽዋ ታንዛኒያ መግባታቸው ተነገረ

Published in News and Events Wednesday, 04 November 2015 19:17

ናይጄሪያዊው የሲናጎግ ቸርች ኦፍ ኦል ኔሽን መሪ የሆኑት ነቢይ ቲቢ ጆሽዋ በአዲሱ የታንዛኒያ ፕሬዚደንት በዓለ ሢመት ላይ ለመገኘት በመዲናይቱ ዶዶማ ሲደርሱ በመንግሥት ኃላፊዎች አቀባበል የተደረገላቸው መሆኑ ተነገረ፡፡ ጥቅምት 23 ቀን፣ 2008 ዓ.ም. ታንዛኒያ የደረሱት ቲቢ ጆሽዋ፣ የፕሬዚዳንቱ አማካሪ በሆኑት ጆን ማጉፋሊ፣ ጃካያ እየለቀቁ ያሉት ፕሬዚደንት እንዲሁም የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትርና የተቃዋሚ መሪ የሆኑትን ኢድዋርድ ሎዋሳ አግኝተው ማነጋገራቸው ከbulawayo24.com የደረሰን መረጃ ያስረዳል፡፡

 

እንደ ደረሰን መረጃው ከሆነ፣ በቅርቡ በታንዛኒያ በተደረገው ምርጫ አሸናፊ የሆኑት ጆን ማጉሊ ከዓመታት በፊት ወደ ናይጄሪያ በመሄድ ቲቢ ጆሽዋን ሲያገኟቸው ለፕሬዚዳንትነት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እንደ ደገፉላቸው ተገልጿል፡፡ ለዚሁ እንደ ማስረጃ ተደርጎ የቀረበውም፣ ማጉሊ እ.አ.አ. በ2011 ከቤተ ሰቦቻቸው ጋር በመሆን ነቢዩንና የሲናጎግ ቸርች ኦፍ ኦል ኔሽን መጎብኘታቸውን የሚያሳይ ምስል መለቀቁ ነው፡፡

 

ይህ የነቢይ ቲቢ ጆሽዋ የታንዛኒያ ጉብኝት ትልቅ ትኩረት የሳበ እንደ ሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ የዚህም ምክንያቱ ነቢዩ በግንቦት ወር በሜክሲኮ ባደረጉትና ከመቶ ኀምሳ ሺህ ሰው በላይ ተግኝቶበታል ከተባለው ጀማ ስብከት በኋላ ከሕዝብ ዕይታ ውጪ ሆነው መቆየታቸው እንደ ሆነ ተነግሯል፡፡

 

ነቢይ ቲቢ ጆሽዋ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ የተነገረ ሲሆን፣ ይህም በአብያተ ክርስቲያናት መካከል ከፍተኛ ልዩነት ፈጥሮ ያለ ጉዳይ መሆኑ ይታወሳል፡፡ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ቲቢ ጆሽዋን ያስመጣ ወይስ አያስመጣ የሚለው ውዝግብ በኅብረቱ ቦርድ አመራር አባላት መካከል ክርክርን ፈጥሮ፣ በመጨረሻም ኅብረቱ ማስመጣት የለበትም የሚል ውሳኔ ላይ ተደርሷል፡፡ ይሁን እንጂ ይህንን የኅብረቱ ውሳኔ ያልተቀበሉ ዐርባ የሚደርሱ ቤተ እምነቶች “የወንጌል ሪቫይቫል ኮንፈረንስ” የሚባል ኮሚቴ በማዋቀር ግለ ሰቡን ለማስመጣት በእንቅስቃሴ ላይ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

Read 7402 times

Nahu's Corner

 

 

 

.

Right Now

We have 30 guests and no members online

About Us

Semayawi Thought is an online magazine published in Amharic and English, focused on contents to spiritual and personal growth.