You are here: HomeNews/EventsThe Movement for African National Initiatives (MANI)

The Movement for African National Initiatives (MANI)

Published in News and Events Tuesday, 08 March 2016 08:23

በትላናንትናው ዕለት በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ Movement for African National Initiatives (MANI) በሚባል ሚኒስትሪ የተዘጋጀ ስብሰባዛሬ ባለው ሁኔታ እግዚአብሔርን መስማትና መታዘዝበሚል መሪ ቃል ተጀምሯል።

 

የዚህ እንቅስቃሴ ዋና አላማ፥በአፍሪካ ደረጃ ያሉ የቤተክርስቲያናት መሪዎችን ለወንጌል ስራ ለማነቃቃትና ለማጠንከር እንደሆነና ትላንት የተጀመረውም ስብሰባ፥ይህንኑ አላማ ከአለም ዙሪያ በተለይም ከፍሪካ አህጉር ለመጡ የቤተክርስቲያን መሪዎችና መጋቢዎች ለማካፈል እንደሆነ ለማወቅ ችለናል።

 

በስብሰባው ላይ የኢትዮጲያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት መሪ ፓስተር ጻድቁ አብዶ ተግኝተው የመክፈቻ ንግግርና የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያቀረቡ  ሲሆን ፥ የኢትዮጲያ ወንጌላውያን ህብረት ታሪክ የጀመረበትን ጊዜና ሁኔታ በማስታወስ  በጊዜው የነበረው የኮሚውኒስት አመራር ብዙ ቤተክርስቲያናትን እንዳዘጋና ይህም ለኢትዮጲያ ወንጌላውያን ቤተክርስቲያን ታሪክ ትልቅ ተግዳሮት እንደነበር በማንሳት፥ዛሬ ግን እግዚአብሔር ጸሎታችንን ሰምቶ፥ቤተክርስቲያን በነጻነት እንደተሰፋፋና አምልኮአችንንም በነጻነት የምናደርግበት ለወንጌል አመቺ ጊዜ ላይ እንዳለን ለእንግዶቹ አስታውቀዋል።

 

ይህ ስብሰባ ሶስተኛው አህጉራዊ የምክክር እንቅስቃሴ ሲሆን፥ ስብሰባውን ለመካፈል ከአለም ዙሪያ የቤተክርስቲያ መሪዎች፥መጋቢዎችና ሚሽነሪዎች ተገኝተዋል።ስብሰባውም ለሚቀጥሉት አምስት ቀናት በዚሁ አፍሪካ ህብረት አዳራሽ እንደሚቀጥል ከአዘጋጆቹ ሰምተናል።

 

Read 3890 times Last modified on Tuesday, 08 March 2016 09:22

Nahu's Corner

 

 

 

.

Right Now

We have 86 guests and no members online

About Us

Semayawi Thought is an online magazine published in Amharic and English, focused on contents to spiritual and personal growth.