You are here: HomeNews/Eventsልዩ የገና መዝሙር ኮንሰርት

ልዩ የገና መዝሙር ኮንሰርት

Published in News and Events Thursday, 01 January 2015 00:00

ድንቅ ስጦታ በሚል ርእስ ልዩ የገና መዝሙር ኮንሰርት ቅዳሜ ታህሳስ 25 ቀን 2007 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ጀምሮ በምስራቅ አዲስ አበባ መሰረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ይካሄዳል። የዚህ የገና መዝሙር ኮንሰርት ዓላማ የሰዎች ሁሉ ዓይኖች ክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ ላይ እንዲሆን፥ ትልቁ ስጦታ እሱ እራሱ እንደሆነ እንዲታወቅና በዕለቱም ሰው እግዚአብሔርን ከመዝሙር አምልኮ ባሻገር በተግባር ወላጅ ያጡና ችግረኛ ሕጻናትን ባለው ነገር ማለትም ጊዜውን፥ እውቀቱን ፥ ገንዘቡን ፥ በሚችለው ሁሉ በመስጠት እንዲያመልክ ነው።

 

ዳዊት ጌታቸው ልዩ በሆነ የሙዚቃ ቅንብር  ከሙሉ ባንድ ጋር በመሆን በአይነቱ ለየት ያለ የገና መዝሙር ኮንሰርት እንደሚያቀርብና በእለቱ የሚሰበሰበው የፍቅር ስጦታ ችግረኛና ወላጅ ላጡ ህጻናት የሚሰጥ ስጦታ እንደሆነ ከዝግጅት ክፍሉ ሰምተናል።

Read 7210 times Last modified on Thursday, 01 January 2015 09:31

Nahu's Corner

 

 

 

.

Right Now

We have 225 guests and no members online

About Us

Semayawi Thought is an online magazine published in Amharic and English, focused on contents to spiritual and personal growth.