ድንቅ ስጦታ በሚል ርእስ ልዩ የገና መዝሙር ኮንሰርት ቅዳሜ ታህሳስ 25 ቀን 2007 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ጀምሮ በምስራቅ አዲስ አበባ መሰረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ይካሄዳል። የዚህ የገና መዝሙር ኮንሰርት ዓላማ የሰዎች ሁሉ ዓይኖች ክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ ላይ እንዲሆን፥ ትልቁ ስጦታ እሱ እራሱ እንደሆነ እንዲታወቅና በዕለቱም ሰው እግዚአብሔርን ከመዝሙር አምልኮ ባሻገር በተግባር ወላጅ ያጡና ችግረኛ ሕጻናትን ባለው ነገር ማለትም ጊዜውን፥ እውቀቱን ፥ ገንዘቡን ፥ በሚችለው ሁሉ በመስጠት እንዲያመልክ ነው።
ዳዊት ጌታቸው ልዩ በሆነ የሙዚቃ ቅንብር ከሙሉ ባንድ ጋር በመሆን በአይነቱ ለየት ያለ የገና መዝሙር ኮንሰርት እንደሚያቀርብና በእለቱ የሚሰበሰበው የፍቅር ስጦታ ችግረኛና ወላጅ ላጡ ህጻናት የሚሰጥ ስጦታ እንደሆነ ከዝግጅት ክፍሉ ሰምተናል።