You are here: HomeNews/Eventsየኢቫሱ የተማሪዎች ምረቃ በዓል ተካሄደ

የኢቫሱ የተማሪዎች ምረቃ በዓል ተካሄደ

Published in News and Events Monday, 30 June 2014 00:00

በኢቫሱ አዘጋጅነት በየአመቱ የሚደረገው የተማሪዎች የምረቃ በዓል እሁድ ሰኔ 22 ቀን, 2006 ዓ.ም በምስራቅ መረተክርስቶስ ቤ/ክ ተካሄደ፡፡ በዘንድሮው መት ወደ 6 ሺህ ሚጠጉ ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች በአገር አቀፍ ደረጃ የተመረቁ ሲሆን በለቱም ከአዲስአበባና አካባቢው የተወከሉ 550 ወንጌላውያን ምሩቃን ተማሪዎች፣ የቤተክርስቲያን መሪዎች ፣ የተመራቂ ተማሪ ወላጆች ፣ የቀድሞ ምሩቃን፣ ተጋባዥ እንግዶች፣ የኢቫሱ ስታፍ እና የቦርድ አባላት በአጠቃላይ ወደ2000 የሚጠጉ ሰዎች ተገኝተዋል፡፡

 

ተማሪዎቹን እግዚአብሔር ስለረዳቸው በማመስገን ፣ ለቤ/ክ በማስረከብ እና ወደ ቀጣይ የህይወት ስምሪታቸው ጸልዮ በመላክ የዘንድሮውም የምረቃ በአል በተሳካ ሁኔታ ተጠናቅቋል፡፡

የትምህርት ልዕቀትን በሚመለከት ከ3.5 በላይ ላመጡ የዲግሪ ተመራቂዎች እና ከ3.75 በላይ ላመጡ የድህረ ምረቃ ተመራቂዎች የማበረታቻ ሽልማት የተሰጠ ሲሆን፤ 4.00 በማምጣትም መስታወት ስምኦን ዋንጫ ተሸልማለች፡፡ 

 

ፍቅሩ ቀና 4.00 ነጥብ በማምጣትና 12 A+ በማስመዝገብ የአመቱ አጠቃላይ የዋንጫ ተሸላሚ ሲሆን እንዲሁም የመጀመሪያው የኢቫሱ ስታፍ የነበሩትና እስካሁንም በንቃት ተሳትፎ እያደረጉ ያሉት ዶ/ር ተከስተ ተክሉ የአመቱ የኢቫሱ ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ ኢቫሱ ከቢብሊካ ጋር በመተባበር የአዲሱ መደበኛ ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ እና በሊሻን አጎናፍር አማካኝነት የምድረበዳው እረኛ የሚለውን መጽሐፍ በትህምርታቸው ብልጫ ላመጡ ተመራቂዎች አበርክቷል፡፡

 

በአሁኑ ጊዜ አኢቫሱ ከ41000 በላይ ወንጌላውያን ተማሪዎችን አቅፎ እያገለገለ ይገኛል። እነዚህ ልጆች የነገ የሃገርና የቤተክርስቲያን ተረካቢ ስለሆኑ ፥ ቤተክርስቲያናትና ምሩቃን በትጋት አብረውን ተማሪዎች ላይ እንዲሰሩ ጥሪ እናደርጋለን ሲሉ የኢቫሱ ዋና ጸሃፊ አቶ ዘላለም አበበ ኣሳስበዋል።

 

 

Read 8000 times Last modified on Wednesday, 02 July 2014 08:18

Nahu's Corner

 

 

 

.

Right Now

We have 239 guests and no members online

About Us

Semayawi Thought is an online magazine published in Amharic and English, focused on contents to spiritual and personal growth.