በእኔ አመለካከት ትርጉማቸዉ በፍጥነት እየተቀየሩ ከመጡ ሃሳቦች መካከል አንዱ “የጦር ሜዳ” የሚለዉ ነው። ቃሉ ለዘመናት ያገለገለዉ ከሰላማዊ ሰዎች መኖሪያ ወጣ ተብሎ ለጦርነት የሚያገለግልን ሥፍራ ለማመልከት ነዉ። የጥንት ጦርነቶች ከከተማ ቅጥሮች ዉጪ ተካሂደዉ፤ ያሸነፈዉ አካል ለምርኮና ለብዝበዛ ወደ ከተሞች ዘልቆ ይገባ ስለነበር ጦርነቶቹ የሚካሄዱበት የተለየዉ ሥፍራ ነበር “የጦር ሜዳ” የሚባለዉ። አጠቃላይ ትርጉሙንና ልምዱን ለማሳየት እንጂ ከዚህ በተለየ መልኩ ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ ያደረጉ ዘግናኝ ጦርነቶችም በሰዉ ልጅ ታሪክ ዉስጥ ነበሩ።
በአጠቃላይ ግን “ጦር ሜዳ የሚሄድ ዘማች” እና “በቤት የሚቀር/በሰላማዊ ቦታ የዘወትር ተግባሩን የሚያከናዉን ዜጋ” የተለያዩ ነበሩ። አሁን እንዲህ ያለ ነገር መቅረቱን በግልጽ እናስተዉላለን። ዓለም በሞላ የጦር ሜዳ ሆናለች። ያለንበት ማንኛዉም ቦታ (የሥራ፣ የገበያ፣ የመዝናኛ ወ.ዘ.ተ.) በቅጽበት ወደ ጦር ሜዳነት ሊቀየር ይችላል። በጥቂት ቀናት ልዩነት የዋሽንግተን የባህር ኃይል መሥሪያ ቤትና የአሁኑ የጎረቤታችን ናይሮቢና ናይጄሪያ ዘግናኝ እልቂቶች ይህንን ያመላክቱናል። ሰዎች በጠዋት ተነስተዉ ወደ ሥራ፣ገበያ፣ መዝናኛ እንጂ ወደ “ጦር ሜዳ” መሄዳቸዉን አላስተዋሉም። በነገራችን ላይ፣ ሰሞኑን እየታየ ባለዉ “ፊልም መሳይ” የሰላማዉያን እልቂት የተሰማኝ ሃዘንና የጸሎት ሸክም በቃሌ ልገልጸዉ አልችልም።
ታዲያ እንዲህ ባለ ዘመን:-
አንደኛ ስለእያንዳንዷ ቀን የሕይወት ስጦታ፤ የሕይወታችንን ባለቤት እንድናመሰግን ሊያደርገን ይገባል። ሕይወትን እንደዘበትና እንደሚገባን ነገር አንቁጠር። በጦር ሜዳ ዓለም የተሰጠንልዩ ጸጋ በመሆኑ ማመስገን ይገባል።
በሌላ በኩል ደግሞ የጌታችን ኢየሱስን ቃል ሊያስታዉሰን ይገባል (ማቴ 24፡6 7)። ጦርና የጦር ወሬ የመምጣቱ አንድ አመልካች አስታዋሽ/ደወል በመሆኑ ነቅቶ መኖርና መጠበቅ ይገባል። “አትደንግጡ” ያለንን ጌታ ታምነን በእምነት “በሞት ጥላ መካከል እንኳን ብሄድ፣ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም” እንላለን። በተጨማሪም ለዘብተኛ መንፈሳዊነትን፣ ማፈግፈግን፣ መንፈሳዊ እንቅልፍን አስወግደን በትጋት ከጌታ ጋር እለት እለት መራመድ ግድ ነዉ። We can not afford to be weak or to backslide! በመጨረሻም ክርስቶስን በግል በማመንና በመከተል መዳን ያስፈልገናል። ጌታን ስናምን ሞት አያስፈራንም፤ ምክንያቱም ከሁለተኛዉ ሞት (ከገሃነም) የተረፍን በመሆኑ። “ሞት ሆይ መዉጊያህ የት አለ” (1ቆሮ 15፡54) በሚል የትንሣኤ እምነት እንመላለሳለን።
በአጠቃላይ የዛሬዉ ምክሬ ይህ ነዉ፡-