ምግባረ ብልሹነት ዛሬ ለቤተ ክርስቲያን ትልቅ ተግዳሮት ሆኗል፡፡ ይህም የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ ዛሬ ያለነው ወንጌላውያን ቤተ እምነቶች “. . . የጠራችሁ እርሱ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተም በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ . . .” (1ጴጥ. 1፥14-15) የሚለውን አምላካዊ ጥሪ/ግብዣ የዘነጋንበት በትኩረትም የማናስተምርበት ወቅት ላይ ነን፡፡ ቅዱሱ ወንጌል በቅድስና መያዝ ያለበት መሆኑን ማስተጋባት ቸል የተባለበት በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የቅድስናን ኑሮ ወደ ጎን የተተወበት ጊዜ ላይ ነን፡፡ “እኔ ከዓለም እንዳይደለሁ ሁሉ እነሱም ከዓለም…