አንድ ሲውድን ውስጥ የሚገኝ መስሪያቤት ለሰራተኞቹ በእጃቸው ውስጥ ማይክሮቺፕ እንዲቀበር አደረገ። ይህ ቺፕ የ radio frequency identification (RFID) ቴክኖሎጂ ሲሆን፥ የአንድ ነጠላ ሩዝ መጠን ያለው ነው። ሰራተኞቹ ይህን በእጃቸው የተቀበረውን ቺፕ በመጠቀም በር መክፈት፥ አድራሻቸውን ማሳየት፥ ፎቶ ኮፒና ሌሎች ማሽኖችን መጠቀም እንደሚችሉና ሙሉ በሙሉ የመታወቂያ ካርድን (ID Card) እንደተካ በምስሉ ላይ ይታያል።