ሪዲምሚዲያ በትንሳኤ ዋዜማ በዓይነቱ ልዩ የሆነ የግጥም ምሽት በገነት ሆቴል አዘጋጅቷል፡፡ የፕሮግራሙ ዓላማ በአዳማ ለሚደረገው ቀጣይ የወንጌል ዐውደ-ርዕይ ገቢ ለማሰባሰብ ነው፡፡ የግጥም ምሽቱ ልዩ ገጣሚያንን፣ አኩስቲክ ሙዚቃና መዝሙሮች የሚቀርቡበት ምሽት ነው፡፡ ፕሮግራሙ ሚያዝያ 3 2007 ዓ.ም ከቀኑ 10፡30 እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት የሚቆይ ሲሆን የዝግጅቱ ቦታ ከሜክሲቆ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ወረድ ብሎ በሚገኘው በገነት ሆቴል ፣ መግቢያውም 200 ብር ነው፡፡ ጓደኞቻችሁን ጋብዙ፤ እናንተም አያምልጣችሁ! ሪዲምሚዲያ ፈጠራ በተሞላበት መንገድ ወንጌልን ለማሰራጨት የተነሱ የፎቶግራፈሮች፣ የፊልም ሰሪዎች፣ የፀሃፊዎች፣ የዲዛይነሮች፣ የደራሲዎችና የስልታዊ አሳቢዎች ስብስብ ነው፡፡ እስከአሁን ድረስ ሪዲምሚዲያ ሁለት የወንጌል ዐውደ ርዕዮችን በአዲስ አበባና በሐዋሳ ከተሞች አዘጋጅቷል፡፡