You are here: HomeTheologyPaulos Fekadu
Paulos Fekadu

Paulos Fekadu

ጳውሎስ ፈቃዱ ባለ ትዳርና የሁለት ልጆች አባት ሲሆን፣ በሞያው መምህር ነው። በነገረ መለኮት እና በኮምፒውተር ሳይንስ፣ ከኢትዮጵያ ሥነ መለኮት ድኅረ ምረቃ ትምህርት ቤት (EGST) እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የማስተርስ ዲግሪዎች ያሉት ጳውሎስ፣ እግዚአብሔርን በአእምሮውም ለመውደድ የሚሻ አማኝ ተደርጎ ቢወሰድ ይመርጣል።

Email: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

“ብቻህን ለመቆም ተዘጋጅ”[1]

Published in Social Issues
Tuesday, 17 July 2018 06:41
 “ሰፊው ሕዝብ ታሪክ ሠሪ ነው!” ይል ነበር ደርግ። በዚህ ዓመት 500ኛ ዓመቱ እየተዘከረ ያለው የማርቲን ሉተር የተሓድሶ እርምጃ ግን ተቃራኒውን ይነግረናል፤ ታሪክን የሚሠሩት ግለ ሰቦች ናቸው።   የኮምዩኒዝም ችግሩ ግለ ሰቡን ማጥፋቱ፣ ግላዊውን ፍጡር ከቁብ ያለ መቍጠሩ ነው። ኮምዩኒዝም የግል ፍላጎት፣ የግል ምርጫ፣ የግል አቋም … የሚባል ነገር የለውም። “ሰፊው ሕዝብ” ግለ ሰቡን ውጦታልና የግላዊው ሰው አቋምና ሕልውና ሚዛን አያነሣም። በአገራችንም ሕገ መንግሥት ይኸው ነው፤ በ“ብሔር፣ ብሔረ ሰቦችና ሕዝቦች” ተውጦ ግለ ሰቡ ሟምቷል። ግለ ሰ...
አስቴር አበበ በቅርቡ ያወጣችው የመዝሙር ሰንዱቅ (አልበም) በስፋት እየተደመጠ ነው። በርካቶችም እጅግ እንደ ወደዱት ይናገራሉ። ለመሆኑ አስቴር ማናት? የት ነው የምትኖረው? ወደ ኢትዮጵያ ለምን አትመጣም? በእነዚህና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ከጳውሎስ ፈቃዱ ጋር በስልክ ያደረጉት ውይይት እንደሚከተለው ቀርቧል።   ጥያቄ፡- እኔን እና አልበምሽን ካስተዋወቀን ነገር ልጀምር። ይኸውም “ክብር የበቃህ ነህ” የሚለው የመዝሙርሽ ርእስ ግራ አጋቢነት ነው። ለምን ይህን ርእስ መረጥሽ? አስቴር፡- “ቀድሞም” የሚለውን ቃል ከፊት ባስገባበትና “ቀድሞም ክብር የበ...

መስቀሉን ማኮሰስ፣ ስቁሉን ማራከስ

Published in Theology
Thursday, 01 December 2016 03:43
የክርስትና እምነት ሁለት እውነቶችን ያስተምረናል፤ በሰዎች ሊታወቅ የሚችል አምላክ መኖሩ የመጀመሪያው ሲሆን፣ በእግዚአብሔር ፊት ብቁ እንዳይሆኑ የሚያደርጋቸው ብልሽት (ውድቀት) በሰዎች ዘንድ መኖሩ ደግሞ ሁለተኛው ነው። የሰውን ውድቀት ሳይገነዘቡ እግዚአብሔርን ማወቅ፣ ወደ ትዕቢት ይመራል፤ እግዚአብሔርን ሳያውቁ የሰውን ውድቀት ማወቅ ደግሞ ወደ ተስፋ ቢስነት ይመራል። ኢየሱስ ክርስቶስን ማወቅ ግን ሁለቱንም በአንድ ጊዜ ወደ መረዳት ያደርሳል።[1] ይህም ነገረ ክርስቶስን (የክርስቶስን ማንነት እና ሥራ) የክርስትና ልብ፣ የክርስቲያናዊ አስተምህሮዎች ...

ደ’ሞ የእግዚአብሔር አቻ ሆንን!?

Published in Theology
Saturday, 30 July 2016 05:08
ኢትዮጵያዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተዘፈቀችባቸው ድብልቅልቅ አስተምህሮዎች ዕለት ዕለት እየተበራከቱ፣ መልኳ ተዝጐርጕሮ አሳሳች ከሆነ ከራረመ። ለሕዝበ ክርስቲያኑ በአብዛኛው የሚቀርብለት፣ ራስን ያለ መጠን በማግነን መለኮት-አከል ለመሆን መንጠራራትን እና ምኞትን ያለ ቅጥ ማሳደድን የሚፈቅድ፣ ራስ መር ትምህርት ነው። ከዚህም በላይ የስሕተቶቹ ሁሉ መነሻና መውደቂያ የክርስቶስ ማንነት ነው፤ ለነገሩማ በታሪክ ውስጥ የተነሡ ዋና ዋና አሳቾች ዋናው ችግራቸው የክርስቶስ ማንነት ነው። በእኛም ዘመን የነጻነቱ ዘመን እንዲህ ዐይነቶቹ መርዛማ ትምህርቶች በዘመናዊው ቴ...

ጤና ቢሱ ነገረ ክርስቶስ

Published in Theology
Saturday, 21 May 2016 07:16
ራሱን ሐዋርያ ያደረገው ዘላለም ጌታቸው (ፖዝ)፣ “ኤክሶደስ ቲቪ ሾው” ከተሰኘ የቴሌቭዥን ፕሮግራም ጋር በቅርቡ ቃል ምልልስ አካሂዷል። በዩቲዩብ በተለቀቀው በዚህ ውይይቱ፣ የተዛቡና ጤና ያጡ ትምህርቶቹ ተቀባይነት እንዲያገኙ በብዙ ሲጥር ታይቷል። “ፓስተር ነኝ” የሚለው ፍሬው ቤዛ ደግሞ፣ “ከእውነት የሚበልጥ እውነት” የሚል ርእስ ሰጥቶ በዚህ ዓመት ባሳተመው መጽሐፍ፣ እንደዚሁ በርካታ ጤና ቢስ አስተምህሮዎችን እያስተላለፈ ነው።   እነዚህ ሁለት ሰዎች ኢትዮጵያዊቷ ቤተ ክርስቲያን ለገባችበት የአስተምህሮና የልምምድ ውጥንቅጥ ማሳያዎች ናቸው ማለት ...
ጉባኤ ለመካፈል ወይም ለአገልግሎት በዕለተ ሰንበት ወደ መካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን የአምልኮ ፕሮግራም ጎራ የሚል ሰው፣ ምእመናኑ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የሚያሰሙትን “የሐዋርያት የእምነት መግለጫ” ያደምጣል። የእምነት መግለጫው ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚናገረው አንቀጽ ላይ፣ “በተሰቀለ፣ በሞተ፣ በተቀበረ፣ ወደ ሲኦል በወረደ …” የሚሉ ቃላትን ይዟል።ሌሎች ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናትም ይህንኑ ይቀበላሉ፡፡   ይህ ብቻ ሳይሆን፣ ጌታ ኢየሱስ ወደ ሲኦል መውረዱን ብቻ ሳይሆን፣ በዚያ ለሚገኙት ነፍሳት ወንጌል መስበኩን የሚናገሩ አማኞችም ...

Nahu's Corner

 

 

 

.

Right Now

We have 15 guests and no members online

About Us

Semayawi Thought is an online magazine published in Amharic and English, focused on contents to spiritual and personal growth.