You are here: HomeSocial Issues Solomon Abebe Gebremedhin
Solomon Abebe Gebremedhin

Solomon Abebe Gebremedhin

ከሁለት ደርዘን ዓመታት በፊት በእግዚአብሔር ቸርነት በተሐድሶ የወንጌል አገልግሎት ውስጥ የዳግም ልደት ብርሃንን ያየው ሰሎሞን አበበ መጋቤ ወንጌል ሲኾን በኢቫንጀሊካል ቲዎሎጂካል ኮሌጅ  (ETC) እና በኢትዮጵያ ድኅረ ምረቃ ነገረ መለኮት ት/ቤት (EGST) የቅዱሳት መጻሕፍት መምህር ነው፤ በየአብያተ ክርስቲያናቱ ምስባኮች በመስበክም ይታወቃል። ሰሎሞን ባለትዳርና የሁለት ሴቶች ልጆች አባት ነው።

Website URL: http://solomonabebe.blogspot.com Email: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

ሲ.ኤስ ሉዊስ እና ኮሮና ቫይረስ

Published in Social Issues
Wednesday, 18 March 2020 07:01
እንግዲህ፥ ኮሮና (COVID-19) እጅግ ከባድና ገዳይ ዓለማቀፍ ወረርሽኝ መኾኑ በዓለም ጤና ድርጅት ከተረጋገጠና ከታወጀ ሰንብቷል። በመኾኑም፥ ማንኛውንም የጥንቃቄ እርምጃዎች ኹሉ መወሰድ ይኖርብናል። ተገቢው ነገር ጥንቃቄ እንጂ ሥጋት አይደለም። ቫይረሱ ያደረሰውንና ሊያደርስ የሚችለውን ጕዳት በማምሰልሰል ልክ ባጣ ፍርኀትና ጭንቀት መርበድበድ አይኖርብንም። ጭንቀት ለነገአችን አንዳች ባናተርፍበትም የዛሬን ሰላማችን ግን ይነጥቀናል። እያንዳንዱ ቀንና ዘመን የየራሱ ሥጋትና ጭንቀት ተሸክሟልና።   የዛሬ 72 ዓመት አካባቢ፥ አቶሚክ ቦምብ ዓለማቀፋዊ ...

“ተያይዘን እንዳንወድቅ”…

Published in Social Issues
Thursday, 04 October 2018 01:59
የዘመን ክፉ   ዘመኑ ክፉ ነው። ዘመኑን ያከፋው በክፉ ሰዎች ስለ ተሞላ ይመስለኛል። በዓለማችን ልዩ ልዩ አቅጣጫዎች የምናየውና የምንሰማው ዜና እጅግ የሚያሠቅቅ ኾኗል። ጽንፈኝነት ተስፋፍቷል። የጥላቻና የምሬት ቅስቀሳዎች ሰላም እያደፈረሱና ዕልቂት እየወለዱ ነው። ግለ ሰባዊ “እንካ ቅመሶች” እና ዐምባጓሮዎች ተባብሰዋል። ማኅበረ ሰባዊ ብጥብጦች በብዛትም በስፋትም ጨምረዋል። ዐይነታቸው ብዙ መጠናቸውም አስፈሪ የኾኑ ፖለቲካዊና ባህላዊ ቀውሶች ተበራክተዋል። ግጭትና ፍጅት፥ ሰቆቃና ዋይታ፥ አድልዎና መፈራረጅ፥ ጥላቻና ነገረኛነት ተስፋፍቷል። ጥፋትን ...
የ“ከፍታ” ተስፋ ያነገበው ሰሞነኛው አገራዊ መሪ ቃል ኹለት ነገር አስታውሶኝ ነበር።   አንደኛው ትውስታዬ፥ “የከፍታ ዘመን ለኢትዮጵያ” የተባለውና በሦስት ዐሠርት ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ [እና ኤርትራ?] ስለሚከሠቱ ነገሮች የሚዘረዝረው የቄስ በልእና ሳርካ ትንቢታዊ ንግር ነው። ታወሰኝ ስላችሁ ራእዩ እውነት ነው ወይም ስሕተት ነው ለማለት አይደለም። መባሉን ብቻ ነው ያስታወሰኝ። “የከፍታ ዘመን ለኢትዮጵያ”።   ኹለተኛው፥ ትዝ ያለኝ ነገር፥ ደራሲ እንዳለ ጌታ ከበደ ከጥቂት ዓመታት በፊት በአንድ የግል ጋዜጣ (መጽሔት) ላይ በትንቢቱ ...

እንባዬን ተዉልኝ

Published in Opinions
Friday, 09 June 2017 13:50
ወገኖች፥ አንዳንድ ጊዜ አልቅሱ፥ አልቅሱ አይላችሁም? የተትረፈረፈ የእንባ ምንጭ አይናፍቃችሁም? የምን የእንባ ዚቅ ነው የምታወራው ካልተባልሁ ነው እንግዲህ። “የሣቅ ነው ዓመቱ” በተባለበት ዘመን ልቅሶን ምን አመጣው? ዐውቃለሁ፤ አንዳንድ አንባቢዎች “ውይ፥ ሲያሳዝን! ... ያልገባው ምስኪን! ... ዝም ብሎ ያላዝናል ...” ማለታቸው አይቀርም። “የከፍታ ዘመን”፥ “የመስፋፋት ዓመት”፥ “የጥርመሳ ጊዜ”፥ “የማለፍና የመብረር ቀናት”፥ “የእልልታ ወራት”፥ “የብዝበዛ ዓመት”፥ “የመውረስና የመሻገር ዘመን”፥ “የሞገስና የቅባት ዓመት” ወዘተ. እየተባለ...
ሆሣዕና፤ እነሆ፥ የዐቢይ ጾም ስምንተኛ ሳምንትና የሕማማት ሳምንት ፤ እንኳን አደረሳችሁ።   ሆሣዕና የዕብራይስጥ ቃል ሲኾን፥ ትርጓሜውም “እባክህ አሁን አድን፥ እባክህ አሁን እርዳ” እንደ ማለት ነው። የኀጢአት ዋጋ የኾነው ሞትና ኵነኔ ካስከተለበት የሕይወት መነፈግ የተነሣ የተሠቃየው የሰው ልጅ ረዳትና መድኅን አስፈልጎት ነበር። ሰው ወደ ራሱ የጽድቅ መፍጨርጨር፣ ጥረት፣ ጥበብና ኀይል ቢመለከት ተስፋ አልነበረውም፤ “የሰውም ማዳን ከንቱ ነው” (መዝ. ፻፰፥፲፪)። ይኸን የአድነኝ፣ የታደገኝ፣ የድረስልኝ ሕቅታውን ወደ ሰማይ እንጂ ወደየትስ ይልክ ...
<< Part One ምገባ ወይስ ምደባ
ለመልእክት መሳከርና መንጠፍ ሌላው ዋነኛ መንሥኢ ገደብ ያለፈ “የምደባ” አባዜ ይመስለኛል። ከዓመት እስከ ዓመት በተጋባዥ አገልጋይ ብቻ መንጋውን ለመመገብ ማሰብ ተገቢ አይደለም። ማኅበረ ምእመኑ ያለበትን አጠቃላይ ኹኔታ በመመልከት ክብካቤና ምሪት መስጠት ያለባቸው መሪዎች ድርሻ ወደየት አለ? መላው ሰንበት በደርሶ ሂያጅ አገልጋይ ተጣቦስ እንዴት ይዘለቃል? አንዲት ስብከት ይዞ ሀገር ካገር መዞርስ ለመንጋው ድርቆሽ ከሚመግብ እረኛ በምን ይለያል? እንደ ወጥ ቀማሽ ጡል ጡል ብለን በቃረምናቸው...

Nahu's Corner

 

 

 

.

Right Now

We have 17 guests and no members online

About Us

Semayawi Thought is an online magazine published in Amharic and English, focused on contents to spiritual and personal growth.