You are here: HomeSermonNegussie Bulcha
Negussie Bulcha

Negussie Bulcha

Website URL: http://www.negussiebulcha.com Email: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

"... ይህ ነገር ሁሉ ለምን ደረሰብን?"

Published in Opinions
Monday, 12 December 2022 06:43
‹‹ አጥብቆ ጠያቂ የእናቱን ሞት ቢረዳም›› እውነቱን አውቆ እርሙን ማውጣት፣ ማድረግ ያለበትንም አስተውሎ ማድረግ ይሻለዋል፡፡ የእኛ አገር ነገር አደናጋሪ፣ አሳሳቢ፣ አስጨናቂ፣ አጠያያቂ ከሆነ ሰነበተ፡፡ በአንድ ወገን ሲቃና በሌላ ወገን ይደረመሳል፣ ዛሬ በሰለ ሲባል አድሮ ቃሪያ ይሆናል፡፡ እፎይታ የሩቅ ህልም እየመሰለ ሄደ፡፡ ውጥረትና ሁካታ የወትሮ ልብስ ሆኑ፤ ጣርና ሲቃ አየሩን ሞሉት፡፡ ለምንድነው ይህ የሚሆነው? ምን ቢሆን ነው የሚስተካከለው? መቼ ነው ይህ አገር አደብ የሚገዛው? ብርቱ ጥያቄ ልቦናችንን ይገዘግዛል፡፡ እንደ አገር ሁ...

የፍቅር ያለህ!

Tuesday, 20 September 2016 15:54
የከተማው ሁሉ መነጋገሪያ ሆኑ፤ በገበያ የነርሱ ወሬ፣ በአምልኮ ሥፍራ የነርሱ ወሬ፣ በየቤቱ የነርሱ ወሬ በቤተ መንግሥት የነርሱ ወሬ፣ በየፍርድ ቤቱ የነርሱ ወሬ፣ በየሰዉ ልብ የነርሱ ወሬ፡፡ ምን ዐይነት ሰዎች ናቸው? አንዴ ጌታ ይሉታል፤ አንዴ መሲሕ ይሉታል፤ አንዴ አዳኝ ይሉታል፤ ሌላ ጊዜ ዳኛ ይሉታል፤ ወዳጅም፣ እረኛም፣ መድኃኒትም ንጉሥም፤ የማይሉት ነገር የለም፡፡ ስለ እርሱ ሲናገሩ ቢውሉ አይደክሙም፡፡ ያገኙትን አጋጣሚ ሁሉ ተጠቅመው ስሙን ያነሣሉ፡፡ ሲናገሩ እዚያው አጠገባቸው ያለ ነው የሚመስለው፡፡ ዋና ከተማቸውን ኢየሩሳሌምን ባጭር ጊዜ በት...
መሳካትን የማይፈልግ ማን አለ? ማንም የለም፡፡ የተሟላ ሕይወት ፍቺው እንደየተርጓሚው ቢለያይም የሰው ልጅ በጠቅላላው በእንጥልጥል ያለችውን ሕይወቱን አረጋግቶ ለማቆም ነው ደፋ ቀና የሚለው፡፡ የተመረጠ በልቶ ማደር ቢሆን ዐይን የገባውን ለብሶ መዋብ ቢሆን ከጎረቤት አንቱታ እስከ ሸንጎ ከበሬታ ሕይወት እንዲሳካለት የማይፈልግ ማነው? ይህ ሁሉ የሕይወትን ሙሉነት አያሳይም ቢባልስ? ሕይወት ተሳካች የምንለው ነፍስ በሰላም ስትረጋ ከአምላኳ ጋር ስትታረቅ ለሕዝብ ጠቃሚና ሁነኛ ሥራ ሲሠራ ነው የተባለስ እንደ ሆነ ይህም ቢሆን ያው የጎደለች ሕይወትን ሌላ ጠለ...
ጓዙን ጠቅልሎ ወደ ውጪ አገር የሚሄድ ጓደኛውን ለመሸኘት ከተሰበሰቡት መካከል የሽኝት ፕሮግራሙን ማጠቃለያ ጸሎት የሚጸልየው ሰው እንዲህ ብሎ ጸልዮአል አሉ፡፡   “ጌታ ሆይ ይህ ወንድማችን በሚሄድበት አገር ቢዚ ከሚባል ጋኔን እንድትጠብቀው እንለምንሃለሁ፡፡”   “ቢዚ” የሚባል ጋኔን መኖር አለመኖሩን መመራመራችንን ትተን ባተሌነት “ቢዚነት” የውጪ አገር አበሳ መሆኑ ቀርቶ ውስጥ አገርም የሚያስጨንቀን ጉዳይ እንደ ሆነ እንቀበል፡፡   በቀጠሮ ብዛት፣ በእንቅስቃሴ ብዛት፣ በጉዳይ ብዛት፣ በሥራ ብዛት፣ በሥራ ውጣ ውረድ፣ በማኅበራዊ ግንኙነት ብዛ...

‹‹ዕርቅ - የጥበብ መንገድ››

Published in Opinions
Tuesday, 01 March 2016 14:13
እኛ በክርስቶስ የምናምን የእግዚአብሔር ቤተሰቦች አንድነትና ስምምነት አጥተን ስንጣላ የሚሆነው ነገር ምን ይመስላል ቢባል፡ በታላቅ ጥበብና ጥንቃቄ በተባለው የሸራ ቅብ ላይ አሮጌ የቀለም ጣሳ ቀድደን ድፍድፉን ቀለም ማፍሰስ ነው፣ ለመብላት ያሰፈሰፉ ሰዎች ዐይኖች በሚቋምጡት በወግ የተሰናዳ የእንጀራ ገበታ ላይ አሸዋ መድፋት ነው፤ ለድል አንድ ምዕራፍ የቀረውን ሯጭ ቋንጃ በስለት መበጠስ ነው፡፡ ጠብ የዓለም ሁሉ ሰቀቀን ነው፡፡ በእግዚአብሔር ቤተሰብ መካከል ጠብ ጉልበት ካገኘ ለምድርዓለም የተሰጣት የተስፋ ብርሃን ተስለመለመ ማለት ነው፡፡   ምን ያ...

ጥልቅ ፍሥሓ

Published in Opinions
Monday, 18 January 2016 11:20
በእግዚአብሔር መደሰት ይቻላል? ማለቴ ልናምነው እንችላለን፤ ልንፈራው እንችላለን፤ ልናገለግለው እንችላለን፤ ግን እርሱን ተድላና ፈንጠዝያ ልናደርገው እንችላለን? በሚሰጠን ስጦታ መደሰት እንችላለን፤ ስሙን በየስፍራው እንጠራለን፤ ግን ራሱን እርሱን ስናስብ ደስታ ጢቅ ያደርገናል?   ይህ ያለንበት ዘመን ለብዙዎች የእንግልትና የሥቃይ የሞቼ ባረፍኩት ዘመን ነው ቢባልም ወዲያውም ደግሞ መግቻ የሌለው የፈንጠዝያ ፍላጎት ነበልባል የሚንቀለቀልበት ተድላ አሳዳጅ ዘመን ነው፡፡ “ስለሌለኝ ነው እንጂ ቢኖረኝ የዐለሙን ሁሉ ደስታና ጨዋታ በአንድ ጆንያ ቋጥሬ ቤ...

Nahu's Corner

 

 

 

.

Right Now

We have 73 guests and no members online

About Us

Semayawi Thought is an online magazine published in Amharic and English, focused on contents to spiritual and personal growth.