ወጣቱ ለአዲስ ነገር ያለውን ጥማት በማየት “ቅልብልብ፣ ለስሕተት አሠራር ክፍት፣ ለቋሚና ዘላቂ ነገር ራሱን የማይሰጥና ተለዋዋጭ” አድርጎ የማየት አዝማሚያ በየትኛውም የዓለም ክፍል ያለ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ የዚህች አጭር ምልከታ ዐላማ፣ የወጣቱን መንፈሳዊ ጤንነትና አካሄድ ማጠየቅ ሳይሆን፣ በዕድሜ ስለጠኑ ግን ደግሞ እውነትን ስለተቀሙ፣ በዘመን ዕድሜ ቆይታ የእውነትን መንፈስ አውልቀው ሐሰትንና አሠራሩን በአጭር ስለታጠቁ፣ በቊጥርም እየበዙ ስላሉ፣ ስለ “ትናንት አባቶች” የዛሬ ስሑታን ነው፡፡ እንደ መርዶ ያህል ነው፤ ሌላውን በመምከሪያ ዘመናቸው የሚ...