You are here: HomeNews/Eventsማኅሌት ለዘማሪዎች ማበረታቻ ሰጠ

ማኅሌት ለዘማሪዎች ማበረታቻ ሰጠ

Published in News and Events Monday, 10 April 2017 03:15

ማኅሌት የመዝመር አገልግሎት ትላንት በምሥራቅ መሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ለአምስተኛ ጊዜ ባካሄደው ዓመታዊ መርሓ ግብሩ፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከወጡ የግል ዘማሪያን አልበሞች መካከል ለሦስቱ ማበረታቻ ሰጠ፡፡ ከግል ዘማሪያኑ በተጨማሪ፣ ከዐርባ ዓመታት በላይ በቡድን ዝማሬ ላገለገሉ የሁለት ቤተ እምነት የዝማሬ ቡድኖች በተመሳሳይ ዕውቅና ሰጥቷል፡፡

 

ከግል ዘማሪያን ሽልማቱን ያገኙት፣ መስከረም ጌቱ፣ በረከት ተስፋዬ እና ሳሙኤል ንጉሤ ሲሆኑ፣ ከቡድን ዝማሬ ደግሞ የአዲስ አበባ ሙሉ ወንጌል መዘምራን እና የአዲስ አበባ መሠረተ ክርስቶስ መዘምራን ቡድኖች ናቸው፡፡

 

የማኅሌት የዝማሬ አገልግሎት የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ፕሮፌሰር ጥላሁን አዳራ ለዘማሪያኑ ዕውቅና የተሰጠባቸውን ዐሥራ ሁለት መሥፍርቶች ያብራሩ ሲሆን፣ በዚሁ መሠረትም ከአንድ መቶ በላይ መዝሙሮች ለግምገማ ቀርበዋል ብለዋል፡፡ ይህንን ግምገማ ያደረጉትም መሥፈርቶቹ በሚጠይቁት የሙያ ዘርፎች የተሰማሩ የተለያዩ ግለ ሰቦች በሰጡት ደምፅ መሠረት በዚህ ዓመት የበለጠ ሊበረታቱና ሊመሰገኑ ይገባቸዋል የተባሉትን እንደመረጡ አያይዘው አስረድተዋል፡፡

 

ማኅሌት የመዝሙር አገልግሎት በመዝሙርና በዝማሬ አገልግሎት ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሠራ ሲሆን፣ ይህ አሁን ያካሄደው ማበረታቻ ሥነ ሥርዐት ለአምስተኛ ጊዜ መሆኑን የአገልግሎቱ ዋና የሥራ አስፈጻሚ መጋቢ መላኩ ይገዙ ገልጸዋል፡፡ የመጀመሪያዎቹ ሦስት ማበረታቻ ሥነ ሥርዐቶች የተካሄዱት በአሜሪካን አገር ሲሆን፣ ካለፈው ዓመት ጀምሮ ዓመታዊ መርሓ ግብሩን በኢትዮጵያ ለማካሄድ በተወሰነው መሠረት ለሁለተኛ ጊዜ እዚሁ መደረጉን አብራርተዋል፡፡

Read 14038 times Last modified on Monday, 10 April 2017 06:14

Nahu's Corner

 

 

 

.

Right Now

We have 23 guests and no members online

About Us

Semayawi Thought is an online magazine published in Amharic and English, focused on contents to spiritual and personal growth.